በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያና የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጅቡቲ ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያና የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጅቡቲ ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያና የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጅቡቲ ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

ከውይይቱ በኋላ ባወጡት መግለጫ፤ አራቱ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት በጋራ ፍላጎታቸውና ጥቅሞች ዙሪያ መምከራቸንና የአፍሪካ ቀንድ ቀድሞ የነበረውን ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ መስማማታቸውን አረጋግጠዋል።

ከኢትዮጵያ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ ከኤርትራ ኦስማን ሳላህ እና ከሶማሊያ አሕመድ ኢሴ በጅቡቲ ተገኝተው ከአቻቸው መሐሙድ አሊ ጋር ዛሬ ጳጉሜ አንድ 2010 ዓ.ም ተወያይተዋል።

ውይይቱን በተመለከተ በጥምረት ባወጡት መግለጫም ፤ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ላይ ባደረጉት ሰፊና በጎ ውይይት የተረጋገጠ ሰላምና ጠንካራ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠር በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።

የቻይና ጉብኝታቸውን በተመለከተ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፤ በሱዳን፣ በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ የተጀመረው ሰላም ወደ መጨረሻው ደርሶ በጅቡቲና በኤርትራ መካከል የነበረውን መጠነኛ ቅራኔ የሚፈታበት ነው ብለዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

የአራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:20 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG