በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጥያቄ የመብት ነው”- የቀድሞ ሠራተኞች


ከሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ድረ ገፅ ላይ የተገኘ ፎቶ
ከሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ድረ ገፅ ላይ የተገኘ ፎቶ

በሥራ ማቆም አድማ ላይ የነበሩትና በኋላም ለእስር የተዳረጉት የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጥያቄ የደሞዝ ጭማሪና የሞያ ማረጋገጫ እውቅን የሚጠይቁ የመብት ጥያቄዎች ናቸው ሲሉ በውጭ ሀገር የሚገኙ የቀድሞ ሠራተኞች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

ሠራተኞቹ አስተዳደራዊ በደል እንዲስተካከልላቸው በመጠየቅ ከዐሥር ዓመታት በላይ ማሳለፋቸውን የተናገሩት እነዚህ የቀድሞው ባለደረቦች ፤ “አሁን ቢያንስ መሰማት እንችላለን” - በሚል ነበር ጥያቄያቸውን ያቀረቡት “ለእስር ተዳረጉ እንጂ”- ብለዋል።

ከታሰሩት ጋር በጋራ አድማ ላይ የነበሩት ሌሎች ሠራተኞች የይቅርታ ደብዳቤ ፈርመው ሥራ መጀመራቸው ታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የሠራተኞቹ ጥያቄ አቀራረብ ሕግን የተከተለ አይደለም ማለታቸው ይታወሳል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።)

“የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጥያቄ የመብት ነው”- የቀድሞ ሠራተኞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:11 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG