የዓረና ትግራይ ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በባለፈው እሁድ ዕለት በማይጨው ከተማ የጠራው የድርጅቱ አባላት ስብሰባ በፀጥታ ኃይሎች ትዛዝ እንደተቋረጠበት ማስታወቁን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
የዛሬው ልዩ ዝግጅታችን መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚኖሩትና ሕብረተሰቡን በመርዳት የሚታወቁት የሐጂ ሐሰን ባድረግ ቤተሰብን ይዟል።
መቐለ ከተማ ውስጥ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሞተር ማምረቻ ፋብሪካ የሞከራ ስራውን ኣጠናቆ ውጤቱን ወደ ገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጿል። ሦስት ደረጃ ያላቸውን ሞተሮችን ማምረቱን የገለፁት የፋብሪካው ሃላፊ በቅርቡ ለሃገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን ለአፍሪካና መካከለኛ ሃገሮች ገበያ እንደሚያቀርብ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ኣሳውቀዋል። ፋብሪካውን የጐበኘው ግርማይ ገብሩ የፋብሪካውን ሃላፊ አነጋግሮ ቀጣዩን ጥንቅር ልኳል።
የጋምቤላ እርሻ ባለሐብቶች የሕብረት ሥራ ማኅበር በማንነታችን ላይ ጫና በመፍጠር እና ከልማት ባንክ ይሠጠን የነበረው ብድር በመቆሙ ምክንያት ትልቅ ችግር ደርሶብናል ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
የትግራይ ክልል ምክር ቤት በአለፈው ሰኞ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአቶ አባይ ውልዱ የቀረበለትን ሹመት አፅድቋል፡፡
የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የስድስት ካብኔ አባላት ሹመት ዛሬ ማፅደቁ ተገለፀ፡፡
በላቀ ልዩ ስራና አገልግሎት የተሸለሙት ከፍተኛ ሃኪሞች 6 ናቸው።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱትን የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ተከትሎ ከታየው የጸጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ ወደ የሚማሩባቸው ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች መሄድ ተስተጓጉለው ከሰነበቱት ተማሪዎች፤ የተወሰኑት ትምህርት መጀመራቸው እየተነገረ ነው።
ትናንትና እና ዛሬ በዓዲግራት ከተማ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የታነጸ ሃያ ሁለት ሜትር ርዝመት ያለው መስቀል ተመርቋል።
አራት ጣልያናዊ እንስቶችና አንድ ኢትዮጵያዊት በጋራ የሚተውኑበት ንግግር አልባ ቴአትር ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ለእይታ ቀርቧል። ቴአትሩ በባሌ ጎባ እና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ነበር ለተመልካች የቀረበው። የቴአትሩ ርእስ በጣልያንኛ ‘ሚራጂ ሚግራንቲ’ የሚል ሲሆን ወደ አማርኛ ሲተረጐም “ከአድማስ ባሻገር” ማለት እንሆነ አዘጋጆቹ ይናገራሉ። ከበታች ያለውን ተንቀሳቃሽ ምስል በመጫን ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ።
ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ባጋጠመው ብጥብጥ ከጐንደር ከተማ፣ ከሰሜን ጐንደር ደንብያ ወረዳ እና ከጃዊ ከተማ የተፈናቀሉ ወደ መቐለ ከተማ መድረሳቸው ተዘግቧል ።
የአሸንዳ በዓል በመቐለ እና በተምቤን በልዩ ድምቀት ተከብሯል።
በኢትዮጵያ የተከሰተው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታን ለመግታት መንግሥት ከዓለምአቀፍና አገር በቀል ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየሠራ እንደሚገኝ ታውቋል።
የመቶ ሚልዮን ብር ነዋይ የፈሰሰበት የጤና ምርምር ተቋም በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ውስጥ ተከፍቷል፡፡
በኢትዮጵያ እርስ በእርስ ጦርነት ወቅት የኖረች አንዲት ወጣት የሂወት ታሪክ ላይ የተሞረከሰ አዲስ ፊልም ቤዛ በመቐሌ ከተማ ተመርቆ በብሔራዊ ደረጃ ለእይታ ቀርቧል።
ትናንት ውቅሮ ከተማ ውስጥ በደረሰ የመኪና አደጋ አምስት የክልሉ የሴቶች ቢሮ ሰራተኞች ህይወታቸው ኣልፉዋል።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰኔ 5 ቀን ጥቃት ሰንዝሯል ብሏል። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የኤርትራ መንግስት ለማጥቃት ያደረገውን ሙከራ ቀልብሰናል ብለዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ