በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩበትን ቀን በተመለከተ ምን አሉ?


በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱትን የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ተከትሎ ከታየው የጸጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ ወደ የሚማሩባቸው ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች መሄድ ተስተጓጉለው ከሰነበቱት ተማሪዎች፤ የተወሰኑት ትምህርት መጀመራቸው እየተነገረ ነው።

አንዳንዶቹም ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት መግቢያ ቀኑን ሲያራዝሙ የቆዩ ናቸው።

አሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ተማሪዎች እስከ አሁን ትምሕርት ያለመጀመሩንና በያሉበት የሚታየውን የጸጥታ ሁኔታ ይገልጻሉ።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሶስት ጊዜ የተማሪዎችን የትምህርት መጀመሪያ ጊዜ ሲያስተላልፉ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት ማብቂያ ገብተዋል።

የቬኦኤ ዘጋቢያችን ግርማይ ገብሩ ደግሞ ከመቀሌ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ትምህት ገበታቸው የተመለሱና አዳዲስ ተማሪዎችን አነጋግሯል።

ተማሪዎቹ ወደ መቀሌ ለመጓዝ ስጋት እንደነበረባቸው ገልጸው፤ አሁን ያለው ሁኔታ ግን ሰላማዊ ነው ይላሉ።

የመቀሌ፣ የዓዲግራትና የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን

“የእንኳን ደህና መጣችሁ” ዝግጅት አድርገውላቸዋል፡፡

የዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩበትን ቀን በተመለከተ ምን አሉ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:46 0:00

XS
SM
MD
LG