በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል የዓረና የስብሰባ ፈቃድ ጥያቄ አልደረሰኝም አለ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዓረና ትግራይ ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በባለፈው እሁድ ዕለት በማይጨው ከተማ የጠራው የድርጅቱ አባላት ስብሰባ በፀጥታ ኃይሎች ትዛዝ እንደተቋረጠበት ማስታወቁን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዶም ገብረሥላሴ ሲናገሩ ስብሰባውን ለማካሄድ ማቀዳቸውን ከአንድ ወር በፊት ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በፁሁፍ አሳውቀናል ብለዋል፡፡

የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘአማኑኤል ለገሠ በበኩላቸው ዓረና ትግራይ ያቀረቡት አቤቱታ በተመለከተ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበት ጊዜ ነው፤ ዓላማው ያልታወቀ ስብሰባ ለማድረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ እኔ ለምመራው ኮሚሽን አልደረሰም ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የትግራይ ክልል የዓረና የስብሰባ ፈቃድ ጥያቄ አልደረሰኝም አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00

XS
SM
MD
LG