በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤተክርስትያን ውስጥ መካነ መቃብር ያሰሩት የሙስሊም ቤተሰብ

  • ግርማይ ገብሩ

ሓጂ ዓብደላ ሓሰን ባድረግ እና ቤተሠቦቻቸው

የዛሬው ልዩ ዝግጅታችን መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚኖሩትና ሕብረተሰቡን በመርዳት የሚታወቁት የሐጂ ሐሰን ባድረግ ቤተሰብን ይዟል።

የቤተሰቡ አባል ሐጂ ዓብደላ ሐሰን ባድረግ ተወልደው ባደጉበት የመቀሌ ቀበሌ 14 ማኅበረሰብን ችግሮች ለመፍታት ከተቋቋመው የመደራጃ ማሕበር ጋር በመተባበር እየሰሩ ይገኛሉ።

ሌላው ቀርቶ ማኅበረሰቡ ያጋጥመው የነበረውን የመካነ መቃብር ቦታ ለመፍታት በከተማዋ የመድሃኒዓለም ቤተክርስትያን ቅጥር ግቢ አስራ ሦስት ትላልቅ የመካነ መቃብር ስፍራ እንዲሰራ ታላቅ እገዛ ማድረጋቸውን የመደራጃ ማኅበሩ ገልጿል።

ግርማይ ገብሩ የማሕበሩ ሊቀመንበር አቶ ገብረኪዳን በርሄንና ሐጂ ዓብደላ ሐሰን ባድረግን ጋብዞ አነጋግሯል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የእርስዎ አስተያየት

አስተያየቶችን ለማየት ይህንን ይጫኑ

XS
SM
MD
LG