የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው መረጃው እንደደረሳቸው ገልፀው፤የገጠር አስተዳዳሪዎችን ጠይቀው ድርጊቱ አለመፈፀማቸውን እንደነገርዋቸው ገልፀዋል።
ግርማይ ገብሩ መቐለ ከተማ ውስጥ ያለፈው የ25 ዓመታት ጉዞ እንዴት ታዩታለችሁ በሚል የተለያ ሰዎችን አነጋግሯል።
በኢትዮጵያ የተቀላጠፈ ትምህርት ለአፍሪካ (ALFA) የተሰኘ የትምህርት መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
የኢትዮጵያ የእርሻና የገጠር ልማት ሚኒስቴር አርሶ አደሮችን በምርምር ስራ ላይ እያሳተፈ መሆኑን ይገልፃል።
በዩኒቨርሲቲው የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችና የምርምር ዳሬክተሮች ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በተከዜ ግድብ ላይ 5 የዓሳ ዝርያዎች መገኘታቸው ገልጿል።
የገበያው ሁኔታ በተለይም የደሮ፣ የበጎችና የፍየሎች ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ዝቅተኛው የደሮ ዋጋ 100 ብር፣ ከፍተኛው 250 ብር መካከለኛው ደግሞ 150 ብር እንደተሸጠ ሸማቾች ይነገራሉ። ፍየል ትልቁ እስከ 5000 ብር ደርሷል።
መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል ህዝቡ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከ31 ዓመታት በፊት ባጋጣመው ከባድ ድርቅና ረሃብ ከህዝቡ ጎን በመቆም ከታደግዋቸው ምግባረ ሰናይ ሰዎች አንዱ ሰር ቦብ ጌልዶፍ እንደሆነ ይታወቃል።
የማኅበሩ አባላት ቤት ለቤት በመሄድ የታመሙትን በነፃ ፈቃዳቸው ለመንከባከብ በሚያደርጉት ጥረት ሌላው ቀርቶ ለሳሙና መግዣ እንኳን እንደሚቸገሩ ወይዘሮ መልክዓ ይናገራሉ።
የመኖርያ ቤቶች ችግር በከፋ መልኩ በሚታይባት የመቀሌ ከተማ ውስጥ ለ24 የተቸገሩ እናቶች የተሟሉ ቤቶች አሰርቶ በነፃ የሚያበረክት ሰው ምነኛ የታደለ ነው ይላል ዘጋብያችን ግርማይ ገብሩ ከከተማዋ በላከው ልዩ ዝግጅቱ።
የስምሪት መለያ ለጥፈን በምንሰራበት ጊዜ የኮንትራት ስራ ብናገኝና ወደሌላ ቦታ ብንንቀሳቀስ የትራፊክ ፖሊስ ያለቦታችሁ ተገኝታቿል በሚል ቢቀጣን መመርያው አያስጥለንም ብለዋል ትናንት።
ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ አስተያየታቸውን የሰጡት የባጃጅ ባለቤቶች እንደሚገልፁት መመርያው የስራ ነፃነትን ይገድባል። የስምሪት መለያ ለጥፈን በምንሰራበት ጊዜ የኮንትራት ስራ ብናገኝና ወደሌላ ቦታ ብንንቀሳቀስ የትራፊክ ፖሊስ ያለቦታችሁ ተገኝታቿል በሚል ቢቀጣን መመርያው አያስጥለንም ይላሉ።
የመድኃኒት ቅመማ እና የሕብረተሰብ ጤና ሳይንስ ባለሞያ አቶ ንጉስ ከሦስት ንጥረ ነገሮች ቀምመው ያዘጋጁት ይህ መድኃኒት በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑን ተረጋግጧል።
የኮቺኔል ትል የሚራባው በበለስ ተክል እንደመሆኑ መጠን በለስ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰውና እንስሳት ምግብነት ስለሚውል ትሉ ተክሉን በአጭር ዓመታት ውስጥ አውድሞታል።
በአከባቢው ለአንድ እናት እና ህፃን ለወር 6.5 ኪሎ ፋፋ እና አንድ ሊትር ዘይት ይሰጣል፤ ይኸውም ለ48 እናቶችና ህጻናት እየተሰጠ እንዳለ ታውቋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ክፍሎም ሃይለ ከህዝቡ እየቀረበ ያለው ቅሬታ ትክክል መሆኑን አምነው እንድያውም ግማሹ የወረዳው ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኝ ተናግረዋል።
ለ87 ሺህ ሰው ከመስከረም ጀምሮ እርዳታ መድረሱን የወረዳው አስተዳዳር አመልክቷል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በበኩሉ ደሞዙ የታገደበት ሰራተኛ የለም፤ ሰራተኞቹ ደመወዝ ያልተከፈላቸው ስራ ላይ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ስርዓት ስላላከበሩ ነው ይላል።
ተጨማሪ ይጫኑ