በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህክምና ባለሞያዎችን ሸለመ


ዶክተር መኮነን ሓጐስ
ዶክተር መኮነን ሓጐስ

በላቀ ልዩ ስራና አገልግሎት የተሸለሙት ከፍተኛ ሃኪሞች 6 ናቸው።

ዶክተር መኮነን ሓጐስ ላፉት 32 ዓመታት በተለይም በቀዶ ጥገና ሙያ አገልግለዋል።

ዶክተር መኮነን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኰለጅ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በአማካሪ ቀዶ ጥገና፣ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሃላፊነት፣ በመምህርነትና በአስልጣኝነት በብቃትና በቅንነት ሰርተዋል።

ዶክተር አበራ አለምነህ በሆሳዕና አጠቃላይ ሆስፒታል እኤአ ከ1986ዓ.ም. እስከ 1989ዓ.ም. በአሉት ጊዜያት በሙያቸው ከማገልገል ጀምሮ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር እስከ መሆን የደረሱና በተለያዩ ፕሮግራሞች የአስተዳደር ስራ ብቃታቸውን በማሳየት አለኝታነታቸውን አስመስክረዋል።

እንዲሁም ዶክተር ዘነበ መላኩ ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮምያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ወረርሽኝን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ እና እልህ አስጨራሽ ስራዎች በብቃት የፈጸሙ ባለሙያ በመሆናቸው ተሸልመዋል።

ሌላው በ1980ዓ.ም በሰሜን ጎንደር መተማ ሆስፒታል ስራ የጀመሩና ከዚያም ቀጥለው በሑመራ፣ ደብረታቦር እና አዲስ አበባ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል በማገልገል ሃላፊነታቸው የተወጡት ዶክተር ኤፍሬም ካሳዬ ተሸላሚ ሆነዋል።

ተመሳሳይ ሽልማትና ክብር ያገኙት ሌላው ባለሙያ ዶክተር አብርሃም ገብረ እግዝኣብሔር ይባላሉ። ዶክተር አብርሃም በተለይም በነገሌ ሆስፒታል በጠቅላላ ሃኪምነት፣ በመቱ ካርል ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ሙያና በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃዎችን ያገለገሉ ናቸው።

ዶክተር ዳዲ ጅማ በተለያ የስራ ሃላፊነት ያገለገሉ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ ሲሆኑ በስራ ዘመናቸው የወባና ሌሎች ቬክተር ወለድ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው አገራዊ ርብርብ የጎላ ድርሻ የተጫወቱ በመሆኑ ሽልማትና ክብር አግኝተዋል።

ግርማይ ገብሩ ከተሸላሚዎች አንዱ ከሆኑት ከዶክተር መኮነን ሓጎስ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ያድምጡ።

የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህክምና ባለሞያዎችን ሸለመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:21 0:00

XS
SM
MD
LG