በአማራ ክልል በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ከተማ አስተዳደር ለ15 ቀናት ያህል መብራት በመጥፋቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ያካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ወደ ግጭት ማምራቱንና ግጭቱን ተከትሎም ከሰልፈኞቹ በአንዳንዶቹ ላይ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸውና በተጨማሪም ከአረርቲ ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ የችፑድ ማምረቻ ፋብሪካ ቃጠሎ የደረሰበት መሆኑን ትናት ምሽት ዘግበናል።
አፍሪካ ውስጥ ካለዕድሜያቸው በሚዳሩ ልጆች ብዛት ምዕራባዊ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሃገሮች ከፍተኛውን ቦታ የያዙ ናቸው።
ያዝነው ወር ኒጀር ውስጥ የተገደለው አሜሩካዊ ወታደር ባለቤት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለማጽናናት በስልክ ባነገሯት ወቅት የሟቹን ባለቤትዋን ስም “ላ ዴቪድ ጆንሰንን ለማስታወስ ሲንተባተቡ በመስማቴ የባሰ እንዳልቀስ አድርጎኛል” ስትል ዛሬ ተናግራለች።
ለ2019 ዳይቨርሲቲ ቪዛ /ግሪን ካርድ ሎተሪ/ ተብሎ የሚጠራው ዩናይትድ ስቴትስ በዕጣ ለውጭ ሃገር ሰዎች ቪዛ የምትሰጥበት መርሃ ግብር አዲስ የማመልከቻ ማስገቢያ ወቅት ዛሬ ተጀምሯል።
በዓለም ዙሪያ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ሴቶች ቁጥር ከወንዶቹ ያነሰ ነው።
የአሜሪካዋ የኔቫዳ ከተማ ግዛት ላስ ቬጋስ ከተማ በአለፈው ዕሁድ ከደረሰው የ59 ሰዎች ህይወት ከጠፋበትና ከ5መቶ በላይ ሰው ከቆሰለበት ዘግናኝ ቅጣት እያገገመች ናት፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ለአሥር ዓመታት በሚስጥራዊ እሥር ቤት ታስረው የቆዩት ሁለት ኤርትራዊያን የቴሌቭዥን ጋዜጠኞች ተስፋ ልደት ኪዳኔና ሳልህ ጋማ በሳምንቱ መጨረሻ መለቀቃቸው ተገለጸ።
በጉጂና በቡርጂ ተዋሳኝ አካባቢዎች ባለፈው ሳምንት በተቀሰቀሰ ግጭት ከቡርጂዎች በኩል አንድ ታዳጊን ጨምሮ ቢያንስ ሦስት ሰው ተግድሎብናል ሲሉ አንዱ የቡርጂ ወረዳ ባለሥልጣንና ሌላ ደግሞ የዓይን እማኝ ነኝ ያሉ ሰው ገልፀውልናል ብዛት ያለው የጤፍ ክምር ብለዋል እማኙ፡፡
የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገሮች የተወሰኑ ፍልሰተኞችን፣ ስደተኞች እና ጥገኝነት ፈላጊዎች እንዲቀበሉ የተመደበውን ኮታ እንዲያከብሩ የህብረቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ። የአውሮፓ ፍትህ ፍርድ ቤት ሃንጋሪና ስሎቫኪያ የኮታ ምደባውን በመቃወም ያቀረቡትን ክስ ውድቅ አድርጎባቸዋል።
"ሀሪኬይን ሃርቪ" የተባለውን ከባድ ንፋስ የሚያነጉደው ዝናብ ተከተሎ በጎርፍ የተጥለቀለቁት የቴክሳስ እና የሉዊዚያን አካባቢዎች የጎርፉ ውሃ ከፍታው እየጨመረ ነው።
ሃሪኬይን ሃርቪ በተባለው በከባድ ንፋስ ታዝሎ የሚወርድ ከባድ ዝናብ የዩናይትድ ስቴትስዋን የቴክሳስ ክፍለ ሀገር ሂዩስተን ከተማ አካባቢ እና በሉዊዚያና ክፍለ ግዛትም አንዳንድ አካባቢዎች በከባድ ጎርፍ ተጥለቅልቀዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ የስደተኛ ማስፈር መርሃ ግብሯ አማካኝነት አምጥታ ለምታሰፍራቸው ስደተኞች የመጀመሪያው የሦሥት ወር ጊዜ መኖሪያ ቤት እና ሥራ እንዲያገኙ፣ የአሜሪካን አኗኗርና ባህል ለማስተዋወቅ ብዙ ርብርብ የሚጠይቅ ጊዜ ነው። በርግጥ በአሜሪካ ማኀበረሠብ ውስጥ በደምብ ተዋሕዶ መኖር እንዲህ በሦሥት ወር ውስጥ የሚያልቅ አይደለም።
ሁለት ትላልቅ የናይሮቢ ሆቴሎች ከኮሌራ በሽታ መቀስቀስ በተያያዘ እንዲዘጉ የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አዘዙ።
"ማንኛዋም የአፍሪካ ሴት ልጅ ስታድግ መሪ የመሆን ብቃት አላት” ሲሉ የማላዊ የቀድሞ ፕሬዚደንት ጆይስ ባንዳ ተናገሩ። ሴት ልጅ ለመሪነት ስትበቃ የምትሰራውን በሚገባ የምትውቅ ትሆናለች ሲሉ አክለዋል። ጆይስ ባንድ ይህን የተናገሩት የመሪነት ብቃት ያላቸውን ሴቶች ሁሉ ካሉበት ተፈልገው እንዲገኙ፣ ስልጠና እንዲያገኙ፣ ማኅበረሠቦቻቸው ውስጥ የበለጠ ንቁ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ የሚጠቅሙ መንገዶችን ይፋ ባደረጉበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው።
የሳውዲ አረብያ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች፣ የባህሬን እና የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሃገሮቻቸው ከካታር ጋር ያላቸውን ውጥረት በተመለከተ ትናንት ካይሮ ላይ ተሰብስበው ተነጋግረዋል።
አሜሪካውያን ሀገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ የተመሰረተችበትን ዕለት በየዓመቱ በዚህ ዕለት እኤአ ጁላይ - 4 ያከብሩታል። ዕለቱ ብሔራዊ የዓመት በዓል ነው። በየቦታው ክብረ በዓላት ይካሄዳሉ፡፡ ሰማዩ በርችት ይንቆጠቆጣል። የቪኦኤው ኣራሽ አራብሳዲ ዋሺንግተን በሚገኘው ብሔራዊ ሞል ተዘዋውሮ ሰዎችን “ዕለቱ ደስ የሚል ክብረ በዓል ነው፣ እንዴት ነው የምታከብሩት?” ብሎ በመጠያየቅ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች።
የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን በአፍሪካ የሳህል አካባቢ ሃገሮች ሽብርተኝነትን ለሚዋጉ ሃገሮች ፈረንሳይ ወታደራዊና የገንዘብ ዕርዳታ እንደምትሰጥ አስታወቁ። የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት በማሊ አምስት ሀገሮች ለሚሳተፉበት ክልልላዊ ፀረ ሽብርተኛ ሠራዊት የምዕራባውያንን ድጋፍ ለማጠናከር የታለመ ጉብኝት አድርገዋል።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም /WFP/ እአአ 2016 የዓለም የርሃብ ይዞታ በተመለከተ የአካሄደውን ግምገማ ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡
በአሜሪካ የዕድሜ ባለጠጋው ቁጥር ከሌላው ጋር ሲነፃፀር እየበዛ ነው።
ካታር ሰላም አስከባሪዎቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ኤርትራ በጋራ ድንበራችን ላይ ያለውን አጨቃጫቂ ግዛት ወርራ ተቆጣጥራለች ስትል ጅቡቲ ከሰሰች።
ተጨማሪ ይጫኑ