በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀሪኬይን ሃርቪ እና ኢትዮጵያውያን


"ሀሪኬይን ሃርቪ" የተባለውን ከባድ ንፋስ የሚያነጉደው ዝናብ ተከተሎ በጎርፍ የተጥለቀለቁት የቴክሳስ እና የሉዊዚያን አካባቢዎች የጎርፉ ውሃ ከፍታው እየጨመረ ነው።

የብሄራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት ጎርፉ ከአሁን ቀደም ያልታየ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን ገልጿል። ቢያንስ ሦስት ሰው ሞቱዋል፣ ከሠላሳ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች በጎርፉ ከተጠቁት አካባቢዎች ወጥተው በየመጠለያው እንዲገቡ ተደርጓል።

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ሠለባዎችን ለማትረፍ በፌደራሉና በክፍለ ሃገሮቹ መንግሥታት እንዲሁም በግል ድርጅቶችና በዜጎች መካከልእየተደረገ ያለውን የዕርዳታ ትብብር እያደነቁ ናቸው።

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በጎርፍ ወደተጠቁት አካባቢዎች ዛሬ ይጓዛሉ ተብሉዋል።

የቪኦኤዋ ዚላቲሳ ሆክ ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ታቀርባለች። ሂዩስተን ከተማ የሚገኝ ምግብ ቤት ብሉ ናይል ባለቤት ወይዘሮ ተናኘወርቅ አምበሉን አነግጋራለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሀሪኬይን ሃርቪ እና ኢትዮጵያውያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG