በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ለ10 ዓመታት የታስሩ ኤርትራዊያን ጋዜጠኞች ተፈቱ


ኢትዮጵያ ውስጥ ለአሥር ዓመታት በሚስጥራዊ እሥር ቤት ታስረው የቆዩት ሁለት ኤርትራዊያን የቴሌቭዥን ጋዜጠኞች ተስፋ ልደት ኪዳኔና ሳልህ ጋማ በሳምንቱ መጨረሻ መለቀቃቸው ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ለአሥር ዓመታት በሚስጥራዊ እሥር ቤት ታስረው የቆዩት ሁለት ኤርትራዊያን የቴሌቭዥን ጋዜጠኞች ተስፋ ልደት ኪዳኔና ሳልህ ጋማ በሳምንቱ መጨረሻ መለቀቃቸው ተገለጸ። የሁለቱን ጋዜጠኞች መለቀቅ ቤተሰቦቻቸውና የሰብዓዊ መብት ተሙውጋቾች አረጋግጠዋል።

ጋዜጠኞቹ እና አንድ ሌላ ኤርትራዊ መለቀቃቸውን ለቪኦኤ ያረጋገጡት የጋዜጠኛ ተስፋ ልደት የቤተሰብ አባል የሆኑ ሰው ሳላህ ጋማ እንዲያውም ወደኤርትራ ተጉዞዋል።

ኬንያና ሶማሊያ ድንበር ላይ እ ኤ አ በ2006 ዓ.ም የተያዙት ሁለቱ ጋዜጠኞች ተስፋ ልደት ኪዳኔ የኤርትራ መንግሥት የቴሌቭዥን ጣቢያ ኤሪ ቲቪ ፕሮግራም አቀናባሪ (ፕሮዱሰር) የነበረ ሲሆን ሳልህ ጋማ ደግሞ ካሜራማን (ቪዲዮ ቀራጭ) ነው።

ስለጋዜጠኞቹ መለቀቅ ከኢትዮጵይም ይሁን ከኤርትራ መንግሥት የወጣ መግለጫም ይሁን አስተያየት የለም።

ሁለቱም መንግሥታት አፍሪካ ውስጥ ጋዘጤኛ በማሰር በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሱ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG