ዋሺንግተን ዲሲ —
ካታር ሰላም አስከባሪዎቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ኤርትራ በጋራ ድንበራችን ላይ ያለውን አጨቃጫቂ ግዛት ወርራ ተቆጣጥራለች ስትል ጅቡቲ ከሰሰች።
ካታር ለአለፉት ሰባት ዓመታት በጅቡቲው ራስዱሜራ ተራራ እና የዱሜራ ደሴት አካባቢ ሰፍረው የቆዩትን አራት መቶ ሃምሳ ወታደሮቿን ባስወጣች በማግስቱ በአለፈው ዕሮቡ ነው የኤርትራ ወታደሮች አካባቢውን መያዛቸውን የጅቡቲ ባለሥልጣናት የተናገሩት፡፡
ካታር ሰላም አስከባሪዎቿን ያሰወጣችበትን ምክንያት ባትገልፅም እርምጃውን የወሰደችው ግን ከአጎራባቿ ከሳውዲ አረቢያ ባላት ዲፕሎማሲያዊ አባጓሮ ኤርትራ እና ጅቡቲ ከሳውዲ ጎን መቆማቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ