በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አረብ ሀገራት በካታር ጉዳይ እየተነጋገሩ ነው

የሳውዲ አረብያ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች፣ የባህሬን እና የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሃገሮቻቸው ከካታር ጋር ያላቸውን ውጥረት በተመለከተ ትናንት ካይሮ ላይ ተሰብስበው ተነጋግረዋል።

የሳውዲ አረብያ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች፣ የባህሬን እና የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሃገሮቻቸው ከካታር ጋር ያላቸውን ውጥረት በተመለከተ ትናንት ካይሮ ላይ ተሰብስበው ተነጋግረዋል።

ባለፈው ወር አራቱ ሃገሮች በጋዝና በነዳጅ ሃብት የከበረችው ሃገር በክልሉ ሽብርተኝነትና ታስፋፋለች ብለው በመወንጀል ከሃገሪቱ ጋር የዲፕሎማሲና የትራንስፖርት ግንኙነቶቻቸውን አቋርጠዋል።

ዶሃ ውንጀላውን ስታስተባብል የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብኛል ስትል ከሳቸዋለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ለግብጹ አቻቸው ስልክ ደውለው ጭቅጭቁ ገንቢ በሆነ ውይይት እንዲፈታ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

የቪኦኤዋ ዚላቲሳ ሆክ ያጠናቀረችው ዘገባ አለ፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አረብ ሀገራት በካታር ጉዳይ እየተነጋገሩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG