በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሂዩስተን ከተማ አካባቢና በሉዊዚያና ክፍለ ግዛት አንዳንድ አካባቢዎች በከባድ ጎርፍ ተጥለቅልቀዋል


ሃሪኬይን ሃርቪ በተባለው በከባድ ንፋስ ታዝሎ የሚወርድ ከባድ ዝናብ የዩናይትድ ስቴትስዋን የቴክሳስ ክፍለ ሀገር ሂዩስተን ከተማ አካባቢ እና በሉዊዚያና ክፍለ ግዛትም አንዳንድ አካባቢዎች በከባድ ጎርፍ ተጥለቅልቀዋል።

በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በሚኖሩበት አካባቢ ሃሪኬይን ሃርቪ ባስከተለው ጉዳት ፈጥኖ ደራሽ ርዳታ ሰራተኞች መውጫ ካጡ ሰዎች የድረሱልን ጥሪዎች በማስተናገድ እጅግ በጣም ተጨናንቀዋል።

የቴክሳስ ክፍለ ሃገር አገረ ገዢ ግሬይግ አበት ከፌዴራሉ መንግስት እየተደረገ ስላለው ድጋፍ አመስግነዋል። ፕሬዚደንት ትረምፕም ሃርቪ ያደረሰውን ጉዳትና የርዳታ እንቅስቃሴ ለመመልከት ነገ ወደሂዩስተን ከተማ እንደሚጉዋዙ ዋይት ሃውስ አስታውቁዋል።

የቪኦኤዋ ዚላቲሳ ሆክ ያጠናቀረችውን ዘገባና መኖሪያቸውን ልቀቁ ተብለው የወጡ የሂዩስተን ከተማ ነዋሪዎችን አስተያየት ጨምራ ቆንጅት ታዬ ዘገባ አጠናቅራለች።

በሂዩስተን ከተማ አካባቢና በሉዊዚያና ክፍለ ግዛት አንዳንድ አካባቢዎች በከባድ ጎርፍ ተጥለቅልቀዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:10 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG