የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፌዴራሉን ምርመራ ቢሮ /ኤፍቢአይ/ን ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚን ከሥራ ኃላፊነት ለማባረር የወሰዱትን የውሳኔ እርምጃ “ትክክል ነው” ሲሉ እየሟገቱ ናቸው።
ቦኮ ሃራም ሠማኒያ ሁለት የቺቦክ ልጃገረዶች ለቀቀ አንድ መቶ አሥራ ሦስት ይቀራሉ
የኤርትራ መንግሥት የታላቁ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ተሸላሚ የሆነውንና ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ መልቀቅ አለበት ሲሉ አንድ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኤክስፐርት አሳሰቡ።
የዓለም የፕሬስ ነጻነት ባለፈው የአውሮፓውያን 2016 ዓመተ ምህረት በአስራ ሦስት ዓመታት ውስጥ ባልታየ ደረጃ አሽቆልቁሉዋል ሲል ጽህፈት ቤቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ዛሬ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርት አስታውቋል።
ወደ ዩጋንዳ ከሚገቡ አዳዲስ ስደተኞች ውስጥ ወዲያ ወዲህ የመዘዋወር ነፃነት ይጠበቅላቸዋል። ሀገሬውም በአብዛኛው ስደተኞችን ተቀባይ ነው። ሰሜናዊ ዩጋንዳ ከሚገኝ የስደተኞች ሰፈር የአሜሪካ ድምጿ ጂል ክሬይግ ስለዚህ ልዩ የሆነ የዩጋንዳ የስደተኛ ፖሊሲ ያጠናቀረችው ዘገባ ቆንጂት ታዮ ታቀርበዋለች
በምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር እየበረከተ የመጣበት ምክንያት ኤልኒኞ ከሚባለው የአየር ንብረት ሁኔታ ጋር የተያያዘ መሆኑን ሳይንቲስቶች አመለከቱ።
ትናንት እሁድ ግብፅ ውስጥ በሁለት ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ቢያንስ አርባ አራት ሰዎች ለገደሉት የቦምብ ጥቃቶች ራሱን "እስላማዊ መንግሥት" ብሎ የሚጠራው ቡድን ኃላፊነት ወሰደ፡፡
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሦስት የአፍሪ ሀገሮችና በየመን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይውት ሊያጠፋ የሚችል ረሃብ ለመግባት የቀረው የአራት ወራት ጊዜ ነው ሲል አስጠንቅቋል።
የመሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ የተመረኮዘው የዓለም ሠላምና መረጋጋት “ደንታ ቢስ የፖለቲካ ጥቅም አግበስባሶች” በሚባሉት አደጋ ተደቅኖባቸዋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዜይድ ራዓድ አል ሁሴን አስጠነቀቁ።
ሶማልያ አዲስ ፕሬዚዳንት መርጣለች፤ ትናንት ነው የሶማሊያ ፓርላማ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድን የመረጣቸው። አዲሱ ፕሬዚደንት የተመረጡት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ መሃሙድን 184 ለ97 በሆነ ድምፅ ብልጫ አሸንፈዋቸው፡፡
“ይህ ትዕዛዝ ስራ ላይ የዋለው ከውጭ ጉዳይ፥ ከመከላከያ፥ ከፍርድና ከአገር ደህንነት ሚኒስተር መሥሪያ ቤቶች ጋር በቂ ወይም ምንም ዓይነት ምክክር ሳይደረግ ነው የሚሉት ሪፖርቶች በተለይ አሳስበውናል። እንዲህ ያለው ችኮላ ውጤቱ ጎጂ ሊሆን ይችላል። በአውሮፕላን ጣቢያዎች የተፈጠረው ትርምስ ትዕዛዙ በሚገባ ያልተጠና መሆኑን ያመለክታል።” የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛ ምክር ቤት የሪፐሊካን ፓርቲ አንጋፋ አባላት ሴኔተር ጆን መኬይናና ሴኔተር ሊንዚግራሃም “ደካማ የኢሚግሬሽን አቁዋም ነው ያላችሁ። ይልቁንስ የእስልምና መንግስት ቡድን ሕገ-ወጥ ኢሚጊሬሽንን እና የድንበር ጸጥታ ላይ ብታተኩሩስ?” ፕሬዝዳንት ትራምፕ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዋይት ሃውስን ለተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ አስረክበው ይሰናበታሉ።
በ2017 ዓ.ም. ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በምታካሂደው ኬኒያ ውጥረቱ እየተባባሰ መጥቷል። በሀገሪቱ ምክር ቤት የምርጫ አፈፃፀም ሕግጋቱን ለመቀየር በቀረበ ሃሳብ ዙሪያ ክርክር በተካሂደበት ጉባዔ ላይ ድብድብ መቀስቀሱ ተዘግቧል፡፡
ዋና መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ(CPJ) ዓመታዊ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችን ቁጥር ቀምሮ ይፋ በሚያደርግበት ዓመታዊ ሪፖርቱ በዚህ ወር በሚጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ 259 ጋዜጠኞች ታስረው እንደሚገኙ አስታውቋል። በዚህ ሪፖርቱ ከአፍሪካ ግብጽ 25 ጋዜጠኞችን በማሰር 1ኛ፣ ኤርትራ 17 ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛና ኢትዮጵያ 16 ጋዜጠኞችን በማሰር ሦስተኛ ሀገር ተብላለች።
በዩናይትድ ስቴትስ ኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሶማሊያዊ ስደተኛ በሚያሽከረክረው መኪና ሰዎችን በመግጨትና በስለት በመውጋት ጉዳት ማደርሱን ተከትሎ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተማሪው ይህን ጥቃት ለማድረስ ምን እንደገፋፋው ለመረዳት አዳግቶት ቆይቷል፡፡
ባለፈው ሳምንት ጋና ውስጥ በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ናና አኩፎ አዶ በሚቀጥለው ወር ቃለ መሃላ ፈፅመው መንበረ ሥልጣን ይረከባሉ።
የጋና ምርጫ ኮሚሽን ትናንት የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊና የምክር ቤት አባላት ምርጫ የድምፅ ውጤት ቀስ በቀስ ይፋ እያደረገ ነው፡፡
ጋናውያን ዛሬ አዲስ ፕሬዚደንት እና የምክር ቤት ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ውለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዓለም ዙሪያ በሠላሳ ሦስት ሃገሮች በከባድ ሠብዓዊ ችግር ላለ ወደዘጠና ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የ22.2 ቢሊዮን ዶላር ተማፀነ፤ ይህ ከምንጊዜውም ግዙፍ የነፍስ አድን እርዳታ ተማፅኖ መሆኑ ታውቁዋል።
የሶማሊያን የፓርላማና የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂደት መጠነ ሰፊ የሙስና አድራጎት እየተፈፀመበት ነው የሚሉ ውንጀላዎች እየተሰሙ ነው፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ