የመንፈቅ ዓመቱ ትምህርት 'ተሠርዞ ግቢውን ለቅቀው ወደ ወላጆቻቸው እንዲሄዱ’ ሲል የአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት 'መወሰኑ አሳዝኖናል’ ያሉ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ቅሬታ አሰምተዋል።
ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አሥመራ ላይ የደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኛነት እየሠራ መሆኑን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ገልጿል።
ኦሮምያ ክልል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት የገባውን ቃል አክብሮ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አስታወቀ።
የኃይማኖት መሪዎች ዛሬ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር/ኦነግን/ና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ኦዴፓ/ን ለመሸምገል ድርድር መጀመራቸው ተዘገበ፡፡
''የህክምና ባለሙያዎች ምንም ያህል ኑሮዋችህ አስደሳች ባይሆን እና ተጎጂ ብትሆኑም እናት እናት ነች፣ ሀገርም ሀገር ነው። የተመመው አባታችን፣ የታመመችው እናታችን ናት እነሱን መርዳት ይኖርብናል - '' ዶ/ር ሰኚ ቀጄላ፡፡ በልጅነቴ ሆስፒታል አካባቢ ተወልጄ ማደጌ፣ የሕሙማንን ችግር ማየቴ፣ ጤናን እንድማር ውስጤ ተፅዕኖ ፈጥሮብኛል። አሁን የሀገሩን ከፍተኛ ነጥብ 3.95 ባስመዘግብም፣ ተስፋ የቆረጥኩበትም ወቅት ነበር።
'አባ ቶርቤ' በሚባል መጠሪያ ምዕራብ ኦሮምያ ውስጥ ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስና በክልሉ ባለሥልጣናት እና በፖሊስ ባልደረቦች ላይ ግድያ የሚፈፅምን ቡድን በቁጥጥር ሥር ማዋል መጀመሩን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
"መንግሥት ጦርነት እያወጀ ነው" ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከሰሰ፡፡ አስመራ ላይ የተደረገው ውል ገቢራዊ እንዳይሆንም መንግሥት እንቅፋት እየሆነ ነው ብሏል።
በምዕራብ ሐረርጌ በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረደ “ጭናክሰን” ውስጥ አዲስ ጥቃት እንደተከፈተባቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች የክልሉን ሰላም በመጠበቅ እና በሌሎች የጋራ ጉዳይ ላይ አብረው ለመሥራት በአዲስ አበባ ባደረጉት ወይይት ተስማሙ።
ግድያ እና መፈናቀል እንዲቆም የሚጠይቅ ሰለፍ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተደረገ። ሰልፈኞቹ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲያመጣ ጠይቀዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
ከመንግሥት ጋር በተደረገ ሥምምነት ወደ ሀገር ገብተው በአርዳይታ የሥልጠና ማዕከል የሚገኘ የኦነግ ሠራዊት አባላት “መንግሥት ለሥልጠና ብሎ እየወሰደብን የሚገኘው ግዜ ረጅም እና ያለአግባብ ነው፤ ወደ ቤተሰቦቻችን እንዲሸኙን እንፈልጋለን” ሲሉ ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) እና ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አብረው ለመስራት የውኅደት ሥምምነት ዛሬ ተፈራረሙ።
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ በተማሪዎች መሃከል ዘውግ የለየ ግጭት ለመቀስቀስ የሚውጠነጠን ሴራ እንቃወማለን፤ ሲሉ ትላንት ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የያሶ ወረዳ ነዋሪዎች፣ ትላንት ሐሙስ ማታ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች፤ ሰዎች በጅምላ መግደላቸውን ገልፅዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የያሶ ወረዳ ነዋሪዎች፣ በቡድን በታጠቁ ኃይሎች ሰዎች በጅምላ እየተገደሉ ነው ሲሉ ገለፁ።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አዲስ አበባ ጉለሌ የነበረውን የቀድሞ ጽ/ቤቱን ከ26 ዓመት በኋላ ዛሬ በይፋ ከፈተ።
በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መካከል ያሉትን ችግሮች እንዲፈታ ጠይቀዋል።
ታሪካዊው የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ከእርጅና ብዛት በመጎዳቱ እድሳት እንደሚያስፈልገው ተደጋጋሚ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።
ሰሞኑን በምዕራቡ የኦሮሚያ ክፍል ዋና መንገዶችን ጭምር የዘጋ እና እንቅስቃሴን የገደበ የተቋውሞ ሰልፍ ተደርጓል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ