በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግጭት የተጠረጠሩ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በማኅበራዊ ሚዲያ ገፃቸው እንዳሰፈሩት፥ ፖሊስን ጨምሮ በአካባቢው የበርካታ ነዋሪዎችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
አቶ አዲሱ አያይዘውም የህግ የበላይነትን የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የፌዴራል መንግሥት የፀጥታ አካላት፣ በኦሮሚያና በቤንሻንጉል አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን ችግር ለመፍታት ታጣቂዎች እንደሚገቡ ትላንት ማስታወቁ ይታወሳል።።
የፌዴራል የፀጥታ አካላት ጣልቃ የሚገቡት፣ ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ክልሎች በቀረበው ጥያቄ መሠረት መሆኑን ብሄራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበር ላይ የሚስተዋሉ ግጭቶችን በማኅበረሰቡ ባህል ለመፍታት እንዲያስችል ከአባ ገዳዎች፣ ኡጋዞች እና የእምነት አባቶች የተውጣጣ ቡድን ችግሮች ወዳሉበት አካባቢ ሊንቀሳቀስ ነው።
በጉዳዩ ላይ ዛሬ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል መግለጫ የተሰጠ ሲሆን አባ ገዳዎች፣ ኡጋዞች እና የእምነት አባቶቹ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ አካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግጭት የተጠረጠሩ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:15 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG