የቡኖ በደሌ ዞን ሠፋሪዎች ለብዙ ዓመታት እየተሰቃየን ነው። የሠፈርንበት መሬት ለግብርና አመቺ ባለመሆኑ አርሰን መብላት አልቻልንም። በረሃብ የሞቱ ሁሉ አሉ። ሰሚ አጣን ሲሉ ተናገሩ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የተጀመረው ለውጥ እንዲጠናከርና የሕግ የበላይነት እንዲከበር ወጣቶችና ሴቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጥሪ አስተላልፏል።
ለተሻለ ሀገር ግንባታ ለመሥራት ከፖለቲካ መጠላለፍ በማውጣት በለውጥ ጎዳና አብሮ መጓዝ አስፈላጊ ነው አሉ ጠ/ር አብይ አሕመድ።
ሀገር በቀል ባህሎችን በማጎልበት ለሀገራዊ ፋይዳ ማዋል አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።
ሰሞኑን በአዲስ አበባ ተከስቶ በነበረ ችግር የሃያ ሥምንት ሰዎች ሕይወት ማጥፋቱን ፖሊስ ገለፀ።
ጂማ ከተማ ላይ ሲካሄድ የነበረው የኦሮምያ ገዥ ፓርቲ የሆነው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ዘጠነኛ ጉባዔ ዶ/ር አብይ አህመድን ሊቀመንበር፣ አቶ ለማ መገርሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ጉባዔው በተጨማሪም ሃምሣ አምስት የፓርቲውን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሰይሟል።
ኦህዴድ በዛሬው ዘጠነኛው ጉባዔው ውሎ አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ አሥራ አራት ነባር የድርጅቱን አመራሮች አሰናበተ፣ ድርጅቱ ስያሜውንም ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በሚል እንዲጣራ ወስኗል።
“የፖለቲካ ድርጅቶች በሰላማዊ መንገድ ተወዳድራችሁ ህዝብ ከመረጣችሁ ለደቂቃም ቢሆን ወንበር ላይ መቆየት እንፈልግም” ሲሉ የኦህዴድ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አሕመድ ዛሬ ጅማ ላይ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦሕዴድ/ "የላቀ ሃሳብ ለበለጠ ድል" በሚል ስያሜ፣ 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ነገ መስከረም 8 በጂማ ከተማ እንደሚከፍት አስታወቀ።
የተጀመረውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግር ሂደት ለማስቀጠል ሁሉም አብሮ እንዲሠራ የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጥሪ አቀረቡ። አቶ ዳውድ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት ፤ የሕግ የበላይነትና የዲሞክራሲ መብት በሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ እጅ ሲገባ ማየት ፍላጎትና ምኞታቸው እንደሆነ ተናገሩ።
በአዲስ አበባ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር የአቀባበል ሥነ ስርዓት ተከትሎ፣ የድርጅቱን ባንዲራ “እስቅላለሁ፣ አትሰቅልም” የሚል አምባጓሮ ላይ የተፈጠረ ግጭት ዛሬም ለሦስተኛ ቀን ቀጥሏል፡፡
የደቡብ ሱዳን ተደራዳሪ ኃይሎች ለአምስት ዓመታት ተቀጣጥሎ የነበረውን ግጭት የሚያከትም ሥምምነት ዛሬ ተፈራረሙ።
ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለተሻለ ሀገር ግንባታ መከፋፋልን በመተው አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ።
በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ ሰዋች ባልታወቁ አካላት መሽት ተገለው እየተገኙ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።
በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ "ሕገወጥ ነው" ያለውን አካባቢ ለማፍረስ በሄደበት ወቅት ከነዋሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች መቁሰላቸው ተገለፀ።
አዲሰ አባበ ውስጥ እያካሄደ ባለው የማጣራት ሥራ ባለቤት የሌላቸውን ሕንፃዎችና ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ማገኘቱን የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የኢድ አል አደሃን በዓል ሲያከብር፣ አንድነቱን በማጠናከር እና ይቅርታን በማብዛት እንዲያከብር ጥሪ ቀርቧል።
አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም አወዛጋቢና ወሳኝ ድርሻ ስታንፀባርቅ ቆይታለች። የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን በማቀፍና በምጣኔ ሀብት ደረጃ በጣም ውድ የተባለች የአዲስ አበባ መሬትን በተመለከተ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አመለካከትና ከግለሰብ እስከ ባለሃብት ፍላጎቶች ይንፀባረቁባታል።
ሁሉም የኦሮሞ ድርጅቶች በአንድነት እንዲሰሩ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጥሪ ቀረበ።
ተጨማሪ ይጫኑ