በጎንደርና በባህርዳር ከተሞች ሰላምና መረጋጋት መስፈን መጀመሩን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። የከተሞቹ እንቅስቃሴም ወደ ቀድሞው ይዞታው እየተመለሰ እንደሆነ ገልጿል።
በባህር ዳር ከተማ ዛሬም ውጥረት እንደነገሠና በአንዳንድ የከተማይቱ ክፍሎች አሰሳና የተኩስ ልውውጥ እንዳለ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
ሕዝቡ ባለቤቱ በማይታወቅና በማህበራዊ ድረ-ገፅ ከሚመራ ሰልፍ ጥሪ ራሱን እንዲቆጥብ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አሳሰቡ።
የነአቶ ጉርሜሳ አያሌው መቃወምያ ውድቅ ተደረገ።
የፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ቀደም ሲል የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግኑኝነት የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ዓቃቤ ህግ የመሰረተበትን የሽብር ወንጀል ክስ እንዲከላከል በየነ።
ጎንደር ከተማ ውስጥ የተቃውሞ ትዕይንተ-ህዝብ ያደረጉ ዜጎች የታሠሩ የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሜቴ አባላት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በነበረው በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ ዐቃቤ ህግ ያዘጋጃቸው ምስክሮች መሰማት እንደማያስፈልጋቸው ፍርድ ቤቱ ወሰነ። ለብይንም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
አራቱን የፈደራሊስ ኮንግረስ አመራር አባላትን ጨምሮ ዘጠኝ እስረኞች በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታወቀ።
በእስር የሚገኙት አራቱ የኦሮሞ ፈዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት የጀመሩት የረሃብ አድማ ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን ማስቆጠሩን የእስረኞቹ የቤተሰብ አባላት ገለጹ።
የፈደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባይ ችሎት የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የአመራር አባል የአቶ ሀብታሙ አያሌው የጉዞ እግድ በተመለከተ ዓቃቤ ህግ ያለውን ክርክር በፅሑፍ እንዲያቀርብ አዲስ ትእዛዝ ሰጠ።
ኢዴፓ ትላንት ይፋ ባደረገው መግለጫ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ የሀገሪቱን ህገ-መንግሥት መሠረት ባደረገ አግባብ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል።ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ብሄራዊ ዕርቅ ወሳኝ መሆኑንም ኣሳስቧል።
አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በእስር የሚገኙ አራት የኦሮሞ ፈደራሊስ ኮንግረስ አመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።
የፈደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ ባለመሟላቱ ምክንያት በአቶ ሀብታሙ አያሌው ላይ በተጣለው የጉዞ እገዳ ውሳኔ መስጠት እንዳልቻለ አስታወቀ። የቤተሰቡ አባላት የተፈጠረው ሁኔታ ቤተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሮብናል ብለዋል።
የቀድሞው የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራር አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ አገር ሄደው ለመታከም የሚያስችላቸውን መረጃ መገኘቱን የቤተሰቡ የቅርብ ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
“በጎንደር ከተማ ላለፉት ሦስት ቀናት የነበረው መነሳሳትና ሁከት የአማራ ሕዝብ ተቃውሞ መገለጫ አይደለም” ሲሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ።
አለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት በኤልኒኖ ምክንያት ከ600 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን መፈናቀላቸውን አስታወቀ።
የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ የነበረው አቶ ሃብታሙ አያሌው የህክምና እርዳታ ሲያገኝበት ከቆየበት ሆስፒታል ዛሬ ወደ ሌላ ስፍራ ለመዛወር መገደዱ ታወቀ።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ዜጎች ለረዥም ዓመታት የኖሩበት ቤት ፈርሶ ለጎዳና ተዳዳሪነት መጋለጣቸውን አጥብቆ ያወግዛል ሲል መግለጫ አወጣ።
ተጨማሪ ይጫኑ