በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦፌኮ አመራርን ጨምሮ ዘጠኝ እስረኞች በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታወቀ


አራቱን የፈደራሊስ ኮንግረስ አመራር አባላትን ጨምሮ ዘጠኝ እስረኞች በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታወቀ።

የረሃብ አድማው ዛሬ ዘጠነኛ ቀኑን መያዙን ምንጮች ተናግረው እስረኞቹ በእጅጉ ከመጎዳታቸው የተነሣ በጉልኮስ እየተረዱ ናቸው ብለዋል።

ቂልንጦ ተብሎ በሚጠራው ማረምያ ቤት በአንድ ክፍል ታስረው የሚገኙት የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት ብቻ እንዳልሆኑ የነዚሁ እስረኞች ቤተሰብ አባላት ይናገራሉ።

የረሃብ አድማውን ከመጀመርያው ቀን አንስቶ በማድረግ ላይ የሚገኙትም የኮንግረሱ አመራር አባላት አቶ ጉሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፡ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች አምስት ግለሰቦች መሆናቸው ምንጮቹ ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የኦፌኮ አመራርን ጨምሮ ዘጠኝ እስረኞች በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG