በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጎንደር ጉዳይ


የጎንደር ከተማ
የጎንደር ከተማ

ጎንደር ከተማ ውስጥ የተቃውሞ ትዕይንተ-ህዝብ ያደረጉ ዜጎች የታሠሩ የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሜቴ አባላት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ሰልፈኞቹ በተጨማሪም የሕወሐት ፀረ-አማራነት ይቁም፤ ጎዳና ላይ የሚፈስሰው የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የእኛም ደም ነው፤ የሙስሊም ኮሚቴ አባላት ይፈቱ፤ ተቃውሟችን ከሕወሐት እንጂ ከትግራይ ሕዝብ አይደለም፤ የሻዕቢያ ተላላኪ ሕወሐት እንጂ ወልቃይት አይደለም የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን ያስተጋቡ ነበር፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሰልፉ ዕውቅና የነበረው ባይሆንም እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ሰው አደባባይ መውጣቱን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ንጉሡ ጥላሁን “ሰልፉ በሰላም የተጠናቀቀው ሕዝቡ ለሰላም ባለው ቀናዒነት ምክንያት ነው” ብለዋል፡፡

የሰልፉን በሰላም መጠናቀቅ የተናገሩት ሌላ የጎንደር አካባቢ ባለሥልጣን በሰልፉ ላይ “ትክክል ያልሆኑ መልዕክቶችን ያዘሉ” ያሏቸው መፈክሮች መያዛቸውና መስተጋባታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የጎንደር ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG