በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢደፓ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ሃቀኛ አጣሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጥሪ አቀረበ


የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ

ኢዴፓ ትላንት ይፋ ባደረገው መግለጫ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ የሀገሪቱን ህገ-መንግሥት መሠረት ባደረገ አግባብ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል።ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ብሄራዊ ዕርቅ ወሳኝ መሆኑንም ኣሳስቧል።

ከዚህም ባሻገር ግጭቱ ተከትሎ የጠፋውን የሰው ህይወት የአካል ጉዳት እና የንብረት መውደም የሚያጣራ ለይስሙላ ሳይሆን ለሃቅ የሚሠራ አጣሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል።ፓርቲው ማንኛውም የሕዝብ ጥያቄ ፍጹም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ መቅረብ እንዳለበት መንግሥትም ጉዳዮቹን በሰከነ መንገድ እንዲፈታና ዘላቂ መፍትሄ ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲንቀሳቀስ ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡን አስታውሶ ለዚህ ጥሪው ግን ትኩረት መነፈጉን ይናገራል።

ኤደፓ በኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶችና ስፍራዎች ለሚነሱ የማንነት ጥያቄዎችና ግጭቶች ምንጫቸው ሀገሪቱ የምትከተለው የፌዴራል አድረጃጀት ነው ሲልም ነቅፉዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ኢደፓ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ሃቀኛ አጣሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጥሪ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG