አዲስ አበባ —
ዛሬ እንደጎበኝዋቸው ያስታወቁት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አካላቸው መዳከሙን እና መጎዳታቸውን ይናገራሉ።አድማውን የጀመሩት እስረኞች ጥያቂያቸው ካልተመለሰ በስተቀር በረሃብ አድማው እንደሚገፉም ተናግረዋል።
ዓቃቤ ህግ ከወራት በፊት በሽብር ወንጀል ክስ ከመሰረተባቸው 22 ሰዎች መካከል የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባላት አቶ ጉሜሳ አያኔው፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላ እና አቶ በቀለ ገርባ በሚገኙበት ማረምያ ቤት የጀመሩት የረሃብ አድማ ሰባተኛ ቀኑን ዛሬ መያዙን የቤተሰብ አባላት ገለጹ።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።