በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስር የሚገኙ የኤፌኮ አባላት የረሃብ አድማ ላይ ናቸው


ofc logo
ofc logo

አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በእስር የሚገኙ አራት የኦሮሞ ፈደራሊስ ኮንግረስ አመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

አድማውን ለማድረግ የወሰኑት በማረምያ ቤቱ አስተዳደር ላይ ላቀረቡት የመብት ጥሰት አቤቱታ ጉዳያቸው የሚከታተለው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም መሆኑን አመልክተዋል።

የኤፌኮ አመራር አባላት አቶ ጉርሜሳ አያሌው፣አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ በቀለ ገርባ ከትላንት በስትያ ከቀትር በኃላ ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የቤተሰቦቻቸው አባላት ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በእስር የሚገኙ የኤፌኮ አባላት የረሃብ አድማ ላይ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG