በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአቶ ሀብታሙ ጉዳይ ዛሬው ውሳኔ አልተሰጠም


የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የነአቶ ጉርሜሳ አያሌው መቃወምያ ውድቅ ተደረገ።

የፈደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በነበረው በአቶ ሀብታሙ አያሌው ላይ የጣለውን የጉዞ እግድ እንዲነሳ ላቀረበው አቤቱታ ዛሬም ውሳኔ አልሰጠም።ከዚህ በኃላ ያለው የፍርድ ቤት ሂደት ለአቶ ሀብታሙ የሚጠቅመው ስላልሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ፍርድ ቤት እንደማይሄዱም ጠበቃቸው አስታወቀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት የነ አቶ ጉርሜሳ አያሌውን የክስ መቃወምያ ውድቅ አደረገ።የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡም ቀጠሮ ቆርጧል።

የፈደራሉ ይግባይ ሰሚ ችሎት አቶ ሀብታሙ አያሌው የጉዞ እግዱ ተነስቶለት ወደ ውጭ አገር ሄዶ እንዲታከም ያቀረበውን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ዓቃቤ ህግ የሰጠውን አስተያየት እንደመረመረም አስረድቷል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በአቶ ሀብታሙ ጉዳይ ዛሬው ውሳኔ አልተሰጠም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG