በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ በኤልኒኖ ምክንያት ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ተገለፀ


ዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት
ዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት

አለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት በኤልኒኖ ምክንያት ከ600 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን መፈናቀላቸውን አስታወቀ።

የጃፓኑ ኮርፐረሽን ፓናሶኒክ ከ2,000 የማያንሱ በፀሀይ ሃይል የሚሠሩ ፋኑሶች ለተፈናቃዮቹ አበረከተ፣ 36,000 ተፈናቃዮች ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

ሚስ ማውሪን ኤቺንግ
ሚስ ማውሪን ኤቺንግ

በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ልዑክ ጽ/ቤት ኃላፊ እና በአፍሪካ ህብረት በምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት የልማት ድርጅት እንዲሁም በአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የድርጅቱ ተወካይ ሚስ ማውሪን ኤቺንግ ዛሬ ረፋድ ላይ የድጋፉ ርክክብ በተከናወነበት ሥነ ሥርአት ላይ ይፋ እንዳደረጉት አለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ባደረገው ቅኝት መሠረት በኤልኒኖ ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ እአአ ከነሃሴ 2014 እስከ ግንቦት 2016 በነበረው ጊዜ አስታት 630,000 ሰዎች ከሚኖሩበት ቦታ መፈናቀላቸውን ገልጿል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ኢትዮጵያ ውስጥ በኤልኒኖ ምክንያት ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG