አዲስ አበባ —
አቶ ሃብታሙ አያሌው ወደ ውጭ አገር ሄዶ ለመታከም የሚያስፈልገውን መረጃ የማሟላት ጥረቱ እንደቀጠለ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ገለጹ።
አቶ ሃብታሙ አያሌው ባጋጠመው ህመም ራሱን ስቶ ካዲስቶ እየተባለ ወደ ሚጠራው ሆስፒታል ገብቶ እስከዛሬ ድረስ የህክምና አገልግሎት ሲሰጠው የቆየ ቢሆንም ከዛሬ በኋላ ሊቀጥል እንደማይችል ሆስፒታሉ ገልጾለታል። አቶ ሃብታሙ አያሌውን በቅርብ ከሚከታተሉት ወዳጆቹ አንዱ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ሆስፒታሉ ወደዚህ ውሳኔ የደረሰው ተገቢውን ህክምና መስጠት ባለመቻሉ መሆኑ ነው።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።