መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት እንዲያጣራ የላኩት ኮሚቴ ዘገባውን አቀረበ፡፡
በመላው ዓለም ከ1 መቶ ሠላሳ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ልጃገረዶች ዛሬም የመማር ዕድል አንደሌላቸው አንድ ጥናት አመለከተ፡፡
የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ፣ ያደረጉት ንግግር ያለፈውን በሚገባ ያልገመገመ እና አዲስ ነገር የሌለበት ነው ሲሉ ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ነቀፉ፡፡
“ዕውቅና ነፍጎናል” ባሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንድ አካል ላይ ክሥ መመሥረታቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እና ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቁ፡፡
በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ተቋም የሦስተኛ ዓመት ተማሪዎች እና በአስተዳደሩ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት እንደተቋረጠ ታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር በደልና ሙስና እንደተስፋፉ ይነገራል፡፡
በየዓመቱ በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አረሲዲ የሚከበረው የእሬቻ በዓል ዛሬ ተከብሯል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደስ በደል እና ሙስና ሥር ሰዷል ሲሉ አንዳንድ የቤተክርስቲያኑ አገልጋዮች ለቪኦኤ ገለፁ፡፡
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ የሞቱትም የተፈናቀሉት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር እየተጣራ እንደሆነ የመንግሥት ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ፡፡
ሰሞኑን በኦሮሚያና በበኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎችና በሌሎችም ሥፍራዎች የተቀሰቀሱ ግጭቶች፣ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄዎች አቅጣጫ ለማስቀየር በመንግሥት የተቀየሰ ዘዴ ነው ሲል መድረክ ከሰሰ፡፡
በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ሙሐሙድ ሰዒድ በኢትዮጵያ ከዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ የወጣውን መግለጫ በተመለከተ የመንግሥትን አቋም ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
"ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሀገራዊ ሕልውናዋ ከምንጊዜውም በባሰ ሁኔታ፣ አደጋ ላይ ወድቋል" ሲል ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ለአራት ዓመታት ከሥልሳ አምስት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጭ የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ እድገት እያገዘ እንደሚገኝ መረጃዎች ይናገራሉ፡፡
በመንግሥት ድጋፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች የምርምር ሥራ የተፈቀደው በጀት የሚመለከተው በአለፈው ዓመት ኅዳር ወር በኋላ የተመዘገቡ የምርምር ሥራዎችን ብቻ ነው ሲሉ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ መሪ አስታወቁ፡፡
ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ /ሰመጉ/ “በድንበር ይገባኛል ጥያቄዎች ሰበብ” የብዙ ሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን አመልክቶ የከፋ ችግር ከመከሰቱ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ጠይቀ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በክረምት መርኃ ግብር ለድህረ ምርቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ለምርምር ሥራ በመንግሥት የተፈቀደውን ክፍያ እንደተነፈጉ የ3መቶ ያህል ተማሪዎች ወኪል ነኝ ያሉ ለቪኦኤ ገለፁ፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ /ኦፌኮ/ በቢሸፍቱ ደብረዘይት ከተማ ባለፈው ዓመት በእሬቻ በዓል ላይ ለሞቱት ሰዎች ተቋቋመ የተባለውን መናፈሻ በመቃወም መግለጫ አሰራጬ፡፡
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር ከ1 መቶ 25 በላይ ደርሷል፡፡
ለአለፉት ሰባት ወራት ያህል ከገዥው ግንባር ኢህአዴግ ጋር ውይይት እና ድርድር ሲያደርጉ ከቆዩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አሥራ ሁለቱ ወደ ፊት ለሚደረግ ድርድር አንድ የጋራ ስብስብ መፍጠራቸውን ይፋ አደረጉ፡፡
አልሸባብ በሶማሊያ ውስጥ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት እንደሚሸነፍ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ዋና አዛዥ ተናገሩ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ