በኦሮሚያ ክልል አያሌ ከተሞች የንግድ ሱቆች ተዘግተው መዋላቸው ታወቀ፡፡ በአንዳንድ ከተሞች የሱቅ ባለቤቶች በግድ እንዲከፍቱ ተደርገዋል ተባለ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በዕለት ገቢ ግብር ተመን ላይ የተሰራው ስሌት አርባ በመቶ ያህል ችግር አንዳለበት አስታወቁ፡፡ “የግንዛቤ፣ የመረጃ እጥረትና ሌብነት” መንግሥታቸውን ዋጋ እያስከፈለው አንደሚገኝም ተናገሩ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥራ ዘጠነኛው ወንጀል ችሎት እነማስረሻ ሰጢ በሚለው መዝገብ በተከሰሱ ሠላሳ ስምንት ሰዎች ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ቃል መስማት ጀመረ።
አራቱ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግሬስ አመራር አባላትን ጨምሮ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ፣ የተበየነባቸው ተጠርጣሪዎች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት አቶ በቀለ ገርባ ያቀረቡትን የዋስ መብት ጥያቄ ዛሬ ውድቅ አደረገ፡፡
የመላው አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና ሠማያዊ ፓርቲ የለገጣፎ፣ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የእምነት ነፃነትን በመጣስ ቤተ ክርስቲያን አፍርሷል ሲል ከሰሰ፡፡
የአቶ በቀለ ገርባ የዋሳትና ጥያቄ ውሳኔ ዛሬም መቋጫ እንዳለገኘ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አስታወቀ። በሚቀጥለው ቀጠሮ ግን ውሳኔውን ለማሰማት ቃል ገብቷል።
በአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄ ላይ ጉዳዩን የሚያየው ፍርድ ቤት ዛሬም ውሳኔ እንዳልሰጠ አስታወቀ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ቤት ስለሞቱት አቶ አየለ በየነ ሞትና የሞታቸውን ምክንያት ከሚመለከተው ሆስፒታል ማስረጃ አንዲያቀርብ፣ ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ጥብቅ ትዛዝ ሰጠ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞውን የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሽን በነፃ አሰናበታቸው፡፡ የወቅቱን የዓረና ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ ጉዳይንም እንዲቋረጥ አዘዘ፡፡
በሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን አመራር አባላት ላይ ዓቃቤ ሕግ የመሰረተውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ለሦስተኛ ጊዜ እንዳይራዘም ጠየቀ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ በቀለ ገርባ በዋስ ሊፈቱ አይገባም የሚል መከራከሪያ አቀረበ፡፡
ዓቃቤ ሕግ በአንድ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ ከመሰረተባቸው ሥምንት ሰዎች መካከል፣ አንድ ተከሳሽ በውል ባልታወቀ ምክንያት መሞቱ ተነገረ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት በዓቃቤ ሕግና አራት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ አመራር አባላትን ጨምሮ፣ በሃያ ሁለት ተከሳሾች መካከል ባለው ክርክር አምስቱን በነፃ አሰናብቷል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋ አካባቢ የሚኖሩት ሕፃናት ትምህርት በገንዘብ እጥረት ሳቢያ አደጋ አንዣቦበታል አለ፡፡
በገዥው ግንባር ኢሕአዴግና በተቀዋሚ ፓርቲዎች መካከል በሚደረገው ድርድር የሚሳተፉም ሆኑ ሌሎች እውቅና ያገኙ ፓርቲዎች ሕጋዊ መሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
ዶ/ር መረራ ጉዲና የቀረበባቸው ክስ የፖለቲካ እንደሆነ እርሳቸውም የፖለቲካ እስረኛ እንደሆኑ ለፍርድ ቤቱ አስታወቁ፡፡
የቱሪዝም ኢንደስትሪ በአፍሪካ እየተስፋፋ የሚሄድና ከሃያ አንድ ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድል በአህጉሪቱ የፈጠረ ዘርፍ መሆኑን አንድ ዓለምቀፍ ጥናት አስታወቀ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ "እነ ኦሊያድ በቀለ" በሚል መዝገብ ከኦነግ አመራር አባላት ጋር ግንኙነት በማደረግ አባላትን በመመልመልና ሌሎችንም ድርጊቶች በመፈፀም የፀረ ዓዋጁን ድንጋጌዎች ጥሰዋል ሲል ሰባት ወጣቶችን ከሰሰ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ