አዲስ አበባ —
መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት እንዲያጣራ የላኩት ኮሚቴ ዘገባውን አቀረበ፡፡
ኮሚቴው በዘገባው አያሌ የኦሮሞ ተዋላጆች እንደተገደሉና በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ዛሬም አድራሻቸው እንደማይታወቅ አመለከተ፡፡ ፓርቲዎቹ ለዜጎች ወቅታዊ እና በቂ ጥበቃ አላደረገም ሲሉም መንግሥትን ወቅሰዋል፡፡
ሁለቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዛሬ በጠሩት ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ በኦሮሚያና በሱማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት እንዲያጣራ የሰየሙት ኮሚቴ ያቀረበውን ዘገባ ጋዜጣዊ መግለጫ መልክ አሳውቀዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ