አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ፣ ያደረጉት ንግግር ያለፈውን በሚገባ ያልገመገመ እና አዲስ ነገር የሌለበት ነው ሲሉ ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ነቀፉ፡፡
በምጣኔ ኃብትም ሆነ፣ በመልካም አሰተዳደር ለውጥ ሊመጣ የሚችለው የሥርዓት ለውጥ ሲመጣ ብቻ ነው ሲሉ አስታወቁ፡፡
በአምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሦስተኛ ዓመት፣ የሥራ ዘመን የመጀመሪያው የጋራ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ንግግር ካደረጉ በኋላ ቪኦኤ የሁለት ተቃዋሚ መሪዎችን አስተያየት ጠይቋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ