"ቶቶ" በተሰኘ አስጎብኚ ድርጅት አማካኝነት፣ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ያቀደ የተመሳሳይ ፆታ ፈፃሚዎች ቡድን፣ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ተቃውሞ ገጥሞታል።
የከምባታ ሕዝብ ኮንግረስ ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትኅ ፓርቲ /ኢዜማ/ ጋር መዋሃዱን ፓርቲው አስታውቋል።
ዓቃቤ ሕግ በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የመሠረተባቸው የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል።
“ፔፕፋር” በተሰኘው መርኃ ግብር ዩናይትድ ስቴትስ ባለፉት 15 ዓመታት ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ኤችአይቪ/ኤድስን ለመቋቋም ዕርዳታ ማዋሏ ተገለፀ፡፡
ከስድስት በላይ በሆኑ ፓርቲዎችና እንቅስቃሴዎች ውኅደት የተቋቋመው ሃገርቀፍ ፓርቲ መሥራች ጉባዔውን ዛሬ ጀምሯል፡፡ መጠሪያ ስሙንም በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በሥልጣን "አላግባብ በመገልገል"ና ከባድ "የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል" ሲል ፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የቀድሞውን የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 ሰዎች ላይ ክሥ መሥርቷል።
ሃያ ስድስተኛው የዓለም ነፃ የፕሬስ ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ መድረኮች መከበር ጀምሯል።
በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ተፈፅመዋል ባላቸው ከባድ የሙስና ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ኃላፊዎችና ሌሎች ተከሣሾችን ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከፍተኛ አማካሪ እንዲሁም ልጃቸው ኢቫንካ ትረምፕ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።
“ከታወቁ ዓለምአቀፍ የሽብር ድርጅቶች ጋር የተቀናጀ የሽብር አድራጎት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመፈፀም ሲዘጋጁ ነበር” የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተይዘው መታሠራቸውንና ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የሃገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቀዋል።
የሥራ ጫናም ሆነ በአገሪቱ ከሚታየው መረጋጋት አንፃር ቦርዱ የምርጫው የጊዜ ወደፊት መገፋት እንለበት ቢያምን ይህን የማድረግ ሥልጣን አለው ወይ በሚል የተጠየቁት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥልጣን “የለውም” ብለዋል አያይዘውም ሊደረግ የሚችለውን አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተጀመሩ ሥራዎችን የሚያግዝ “ፍትህ” የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክት በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ይፋ ተደረገ።
"የሰው ሃብት ልማት ለጤና አገልግሎት" በተሰኘው ፕሮጄክት ኢትዮጵያ ወደ ሃምሳ ሺህ የሚጠጉ ባለሞያዎችን ማፍራቷ ተነገረ።
የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) “ከአርበኞች ግንቦት ሰባት የአንድነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ጋር ተፈፅሟል” የተባለውን ውኅደት እንደማያውቀው ገለፀ።
ስድስት ፓርቲዎች አንድ ሃገራዊ ፓርቲ ለመመሥረት ተስማሙ።
የዜጎችን መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ማስከበር የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር መሆኑ ተዘንግቷል ሲል ወቀሳ ያሰማው የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ችግሩ አስቸኳይ ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስቧል። የመንግሥት ባለሥልጣናት ለመብቶች ጥሰት ዋና ተዋናዮች ናቸው ሲልም አማሯል።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ በደቡብ ኢትዮጵያ በአያሌ አባሎቹና ሌሎች ዜጎች ላይ ህገወጥ እስራትና እንግለት የተፈፀመባቸው እንደሆነ አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ የተፈራረሙት የአሰራር ቃል ኪዳን ሰነድ፣ በአይነቱ ልዩ እንደሆነ ተነገረ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ ዓመት 8.3 ሚሊዮን ሰው አስቸኳይ ምግብ ነክና ሌላ ዕርዳታ የሚጠብቅ እንደሆነ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሺን ይፋ አደረገ።
በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት ዓለማቀፋዊነትን ለማጠናከርና የትምህርቱን ጥራት ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ዕርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ አስታወቁ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ