በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በዜጎች ደህንነት ላይ የተባባሰ ሁኔታ ለማምጣት ብለን ምርጫ አናደርግም። ምርጫ የተሻለ ነገር ለማምጣት ነው መደረግ ያለበት” የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ

ፎቶ ፋይል ፡ ቦርዱ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት እና በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሠራር ሥርዓት ቃል ኪዳን ባፀደቁበት ወቅት
ፎቶ ፋይል ፡ ቦርዱ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት እና በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሠራር ሥርዓት ቃል ኪዳን ባፀደቁበት ወቅት

የሥራ ጫናም ሆነ በአገሪቱ ከሚታየው መረጋጋት አንፃር ቦርዱ የምርጫው የጊዜ ወደፊት መገፋት እንለበት ቢያምን ይህን የማድረግ ሥልጣን አለው ወይ በሚል የተጠየቁት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥልጣን “የለውም” ብለዋል አያይዘውም ሊደረግ የሚችለውን አብራርተዋል።

የሥራ ጫናም ሆነ በአገሪቱ ከሚታየው መረጋጋት አንፃር ቦርዱ የምርጫው የጊዜ ወደፊት መገፋት እንለበት ቢያምን ይህን የማድረግ ሥልጣን አለው ወይ በሚል የተጠየቁት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥልጣን “የለውም” ብለዋል አያይዘውም ሊደረግ የሚችለውን አብራርተዋል።
”ምርጫ ለማድረግ ያህል አናደርግም።ምርጫ በዜጎች ደህንነትና ሕይወት ላይ የተባባሰ ነገር ለማምጣት ብለን አናደርግም። ምርጫ የተሻለን ነገር ለማምጣት ነው መደረግ ያለበት። እስካሁን ከተደረጉ ምርጫዎች በአብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ተአማኒነት ያገኘ እንዲሆን አድርገን ለሱ የሚያስፈልጉንን ነገሮች በኛም ፣ በተሳታፊዎችና በሰላሙ ሁኔታ መሬት ላይም መኖራቸውን አረጋግጠን ነው የምናደርገው። “ ብለዋል
አያይዘውም “የኛ ዝግጅት ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ፣ የሌሎች ተሳታፊዎች ያሉበት ሁኔታ እንዴት እንደሆነ እና ያለው ደግሞ የሰላም ሁኔታ ምርጫን ለማድረግ የሚያስችል ነው ወይ? የሚለውን ግምገማ አይተን ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ማድረግ አንችልም ብለን የምናምን ከሆነ ይህንኑ በዝርዝር አስቀምጠን ለሚመለከተው አካል በጥያቄ እናቀርባለን” ብለዋል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዜግነትና በመራጮች ትምሕርት ረቂቅ መመሪያ ላይ ከሲቪክ ማሕበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG