ከታኅሣሥ አጋማሽ ጀምሮ በኦሮምያ የተለያዩ ከተሞች የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን፣ በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ አካባቢ በፌደራልና መከላከያ ቁጥጥር ስር መዋሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኦሮመኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ተናግረዋል፡፡ ጽዮን ግርማ አጠናክራዋለች፡፡
ኢሳያስ ተስፋማሪያም የአስመራ ከተማን ጥናታዊ ፊልም ሰርቶ ለእይታ አቅርቧል።
አስመራ በዩኔስኮ UNESCO የአለም ታሪካዊ ስፍራዎች ወይም “World Heritage”፤ ህንጻዎቿን፣ ታሪኳን እና የግንባታ ውበቷን ልትመዘገብ እጩ ሆናለች።
ተፈራ ሃይሉ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማደጎ የሚመጡትን ህፃናትና ወጣቶች ከኢትዮጵያነታቸው ጋር የመተዋወቂያ መድረክ ይሆን ዘንድ ኔትዎርክ ኦፍ ፋሚሊ ሰርቪስ ፕሮፌሽናልስ የተሰኘ ገባሬ ሰናይ ድርጅት አቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ድርጅቱ በአሜሪካን ሃገር ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የማደጎ ልጆች የኢትዮጵያን ታሪክና ባህል በማስተማር ላይ ይገኛል። የማህበራዊ ሚድያ ፌስቡክ በመክፈት ልጆቹ እርስ በእርስ ችግሮቻቸውን እንዲመካከሩና እንዲፈቱ የመወያያ መድረክ ከፍቷል።
አምበር ስታይም የተወለደችው በጎንደር ደብረታቦር ከተማ ነው። የሶስት አመት ልጅ እያለች ከመሬት መጫወቻ መስሏት ያነሳችው ቦንብ ፈንድቶ ሁለት እጆቿን አሳጥቷታል። በዚህ ምክንያት የተለየ አርዳታ ፈላጊ ሆነች። ኢትዮጵያ በሚገኘው የክርስቲያን የህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ከኖረች በኃላ ለስራ ኢትዮጵያ ይኖሩ ከነበሩት ከአሜሪካውያኑ የማደጎ ወላጆቿ ጋር ወደ አሜሪካ መጣች።
አምበር ስታይም የተወለደችው በጎንደር ደብረታቦር ከተማ ነው። የ3 አመት ልጅ እያለች ከመሬት መጫወቻ መስሏት ያነሳችው ቦንብ ፈንድቶ ሁለት እጆቿን አሳጥቷታል።
ሳራ ነጋሽ የተወለደችው በአዲስ አበባ ነው ከናትና ከአባቷ እንዲሁም ከሁለት ታላላቅ እህቶቿ ጋር ያለችግር ትኖር ነበር። የእናትና የአባቷ ድንገተኛ ተከታትሎ መሞት እሷን ከነ እህቶቿ እሰው እጅ ላይ ጣላቸው፡ ሳራ አሁን በማደጎ ወላጆቿ ቤት በአሜሪካን ሃገር መኖር ከጀመረች 12 አመት ሆኗታል።
ሳራ ነጋሽ ወደ አሜሪካን ሃገር መኖር ከጀመረች አመታትን አስቆጥራለች። በማደጎነት ወደ አሜሪካ ያመጣቻት አሜሪካዊት እናት ሳራ እንዳሰበቻት መልካም ወላጅ ልትሆንላት ስላልቻለች በሊሎች ፈቃደኛ ወላጅ አሳዳጊዎቿ ቤት መኖር ጀምራለች። "አሁን ያለሁበት ቤት ውስጥ ደስተኛ ነኝ" ትላለች ሳራ።
ግዙፍ የኾኑ የመጠጥ አምራች ኩባንያዎች ፊታቸውን ወደ አፍሪካና ኢትዮጵያ ገበያ አዙረዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው በኢትዮጵያ የመጠጥ ማስታወቂያ ገደብ እየተደረገበት አይደለም ይላሉ፡፡ ብስራት ተሾመ፣ቁምላቸው ዳኜ፣አሌክስ አብርሃም እና አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ፡፡ በጉዳዩ ላይ በየሞያቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
"የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ሽፋንና ጥራት በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ምን ይመስላል?" በሚል መነሻ ሐሳብ ይህ ዘገባ በአማራ፣በአፋር እና በኦሮሚያ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት መምሕራንን ስለ ትምሕርት ጥራቱ ይጠይቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ያጠናው ጥናት በዘገባው ተካቷል፡፡
ሄዘር ማክስዌል አሜሪካዊት የጃዝ ሙዚቃ ድምፃዊና አለም አቀፍ የባህል ሙዚቃ አጥኚ ናት። በVOA በአፍሪካ የሬድዮ ፕሮግራም “Music Time in Africa” ሙዚክ ታይም ኢን አፍሪካ በተሰኘው የሬድዮ እና የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ በማዘጋጀትም ትታወቃለች።
“Young Ethio-jazz Band” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ተወልደው ያደጉት በዩናይትድ ስቴትስ ኦክላንድ ካሊፎርኒያ ነው። እድሜያቸው ከዐስራ ሦስት እስከ ዐስራ ስምንት የሆኑት አነዚህ ወጣቶች በጋራ ሙዚቃን መጫወት የጀመሩት የዛሬ አራት ዓመት ነው።"ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ" ይላል ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ።
ደራሲ እና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት የሚጻፉ አንዳንድ መጽሐፎች በሕብረተሰብ መካከል፣ በተለይ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር የሚያላሉ፣አልፎ አልፎ ደግሞ እንዲበጠስ የሚያግዙ አስተያየቶችን እና ሐሳቦችን አያለሁ፡፡”ይላል፡፡
የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉ ያስከተለው ተቃውሞን ተከትሎ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - ኦሕዴድ ዕቅዱን መሠረዙ ይታወቃል፡፡በርካታ አድማጮች በዕቅዱና ዕቅዱን ተከትሎ በተነሣው ተቃውሞ ዙሪያ ጥያቄዎች ልከውልናል፡፡የጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን ሁለት ምሑራን ጋብዟል፡፡
ኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ሚዲያን እንዴት ይጠቀሙበታል? እንዲሁም ታዋቂ ኢትዮጵውያን እና የማያውቁት የፌስቡክ ገጾቻቸው በሚል ርእስ ጽዮን ግርማ ውይይት አዘጋጅታለች፡፡ እንዳልካቸው ኀይለ ሚካኤል፣ የትነበርክ ታደለ፣በእውቀቱ ስዩም ፣ ሳያት ደምሴ፣ አምለሰት ሙጬ እና ኤልሻዳይ ነጋሽ በዚህ ዘገባ ተካተዋል፡፡
"ይህን መንግሥት ከሌሎቸ መንግሥታት ለየት የሚያደርገው፤ ‘እኔ ይህን ያሕል ሞተብኝ’ ብሎ ከተሰላፊዎቹ እኩል ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባል" ከሕግ ባለሞያ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር የተደረገ ቃል ምልልስ (ክፍል ሁለት)
አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።የሕግ አስተማሪና ተመራማሪም ናቸው። በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በድጋሚ ስላገርሸው ተቃውሞ እና የመንግሥት ምላሽ፤ ከሕግ አኳያ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡
“ሃብት ያለው ሰው አይታሰርም። ተፈርዶባቸው እስር ቤት ያሉ ባለ ሃብት መንገድ ላይ ሲሄዱ ሌላ ሰው ገጭተው ሌላ ክስ ተመሠረተባቸው። አቃቤ ሕግ ምሥክር ማስፈራራት የሃሰት መረጃ ማስጠናት። በጥናቱ ካገኘናቸው ውስጥ ናቸው።” አቶ ተካ ገብረ የሱስ፤ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዲሬክተር።
ዶ/ር ፍቅሩ ማሩና ሌሎችም ከሙስና ጋር በተያያዙ ክሦች እሥር ቤት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ጉዳይ ለፊታችን ማክሰኞ፤ ጥቅምት 9/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡ ጠበቆቻቸው ደንበኛቸው የተከሰሱበት መዝገብ አብረዋቸው ከተከሰሱት ሰዎች ጉዳይ ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ ተነጥሎ እንዲወጣና እንዲታይ እየጠየቁ ነው፡፡
Dr. Fikru Maru's Case in Ethiopia - 10-17-15 /mp3 audio: length 30'16" size 27.7mb/
ዶ/ር አምባዬ ወልደ ሚካኤል የማሕጸንና ጽንስ ባለሞያ ናቸው፡፡ሥራ በጀመሩበት አዲስ አበባ ፌስቱላ ሆስፒታል ዐስራ አራት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በዚህ ቆይታቸው በሞያቸው ከሚያገለግሏቸው ሴቶች በተጫማሪ በሆስፒታሉ ውስጥ አንድ ቡድን በማዋቀር ከአዲስ አበባ ውጪ በሦስት ቦታዎች የፌስቱላ ሕክምና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ማዕከላትን አቋቁመዋል፡፡
ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገሮች የመጡ ወደ 900 የሚሆኑ ፍልሰተኞችና ስደተኞች፣ በደቡብ ጣልያን የተባበሩት የአውሮፓ የባሕር ሃይሎች ከመስመጥ አድነዋቸዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጅያ ድርጅትከፍተኛ ኮሚሺነር አንቶንዮ ጉቴረስ በግጭት ምክንያትና የሚደርስባቸዉን ግፍ ሸሽተዉ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እጅግ መጨመር፣ የተራድኦ ድርጅቶች በገንዘብ እጥረት እጃቸዉ ታሶሮ እርዳታ ሊያቀርቡ ያልቻሉበት ጊዜ ጋር መገጣጠሙን በመጥቀስ አስጠነቀቁ።
ተጨማሪ ይጫኑ