በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመጠጥ አምራች ኩባንያዎቸ ወደ ኢትዮጵያ ማተኮርና የማስታወቂያ ገደብ


ብስራት ተሾም፣ቁምላቸው ዳኜ፣ አሌክስ አብርሃምና አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ
ብስራት ተሾም፣ቁምላቸው ዳኜ፣ አሌክስ አብርሃምና አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ

ግዙፍ የኾኑ የመጠጥ አምራች ኩባንያዎች ፊታቸውን ወደ አፍሪካና ኢትዮጵያ ገበያ አዙረዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው በኢትዮጵያ የመጠጥ ማስታወቂያ ገደብ እየተደረገበት አይደለም ይላሉ፡፡ ብስራት ተሾመ፣ቁምላቸው ዳኜ፣አሌክስ አብርሃም እና አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ፡፡ በጉዳዩ ላይ በየሞያቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ቢራን ጨምሮ የአልኮል መጠጥ አምራች ግዙፍ የውጭ ኩባንያዎች እንዲሁም ሀገር በቀል ድርጅቶች ፊታቸውን ወደ አፍሪካ ገባያ እያዞሩ ነው፡፡ ለዚህ ገበያ ከተመረጡት ሀገሮች ደግሞ ኢትዮጵያ አንዷ የኾነቸ ትመስላለች፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በርካታ የአልኮል መጠጥ አምራች ድርጅቶች በከፍተኛ ፉክክር ወደ ገበያ እየገቡ ነው፡፡ ለምን? የልማት ሥነ ምጣኔ ሃብት ባለሞያው ብስራት ተሾመ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

"የመጠጥ አምራች ኩባንያዎቹ መበራከታቸውን ተከትሎ የሚደረጉ የማስተዋወቅ ሥራዎች ገደብ አልባ በመኾናቸው ትውልድን የማበላሸት ስጋት ናቸው" በሚል የሚከራከሩ አሉ፡፡ ለመኾኑ በኢትዮጵያ ቢራን ጨምሮ የአልኮል ማስታወቂያ ሕግ ምን ይላል? ሕጉስ ምን ያህል ይከበራል? ለሚሉት ጥያቄዎች የሕግ ባለሞያው አቶ ቁምላቸው ዳኜ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

ባደጉት ሀገራት ዕድሜው ከሃያ አንድ ዓመት በታች የኾነ ማንኛውም ሰው የአልኮል መጠት ገዝቶ መጠጣት አይፈቀድለትም፡፡ በዚህ ዕድሜ ላይ ያለ ማንም ሰው መጠጥ ሲገዛም ኾነ በዚህ ዕድሜ ክልል ላይ ላለ ሰው መጠጥ ሲሸጥ የተገኘ በወንጀል ተከሶ ይቀጣል፡፡ የመጠጥ ሻጮቹም በዚህ ሲደራደሩ አይታዩም፡፡ የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎችም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ላይ ማተኮር እንደሌለበት ይደነግጋል፡፡ ይህም ይተገበራል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው ኹኔታ ግን ከዚህ የተለየ እንደኾነ ጉዳዩን በትኩረት የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ ሙግቱን በተከታታይ በማቅረብ የሚታወቀው የፌስ ቡኩ አሌክስ አብርሃም ነው፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያ አሌክስ አብርሃም በሚለው ስሙ በተለይም በፌስ ቡክ በሚያቀርባቸው የጹሑፍ ሥራዎቹ ይታወቃል፡፡ ለአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎች ገደብ አለመደረጉ ትውልድን ይጎዳል ሲል ይከራከራል፡፡ አስታያየቱን አካፍሎናል፡፡

ሌላው አስተያየት ሰጪ ከሃምሳ ዓመት በላይ የማስታወቂያ ሥራ ልምድ ያላቸው አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ ናቸው፡፡ መጠጥ ወጣቶችን ይጎዳል ብለው ስለሚያምኑ በዚህን ያህል የሥራ ዘመናቸው አንድም የአልኮል ማስታወቂ ሠርተው እንደማያውቁ ይናገራሉ፡፡ ሁሉም በዚህ ዘገባ ተካተዋል፡፡ ዘገባው የሠራችው ጸዮን ግርማ ነች፡፡

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

የመጠጥ አምራች ኩባንያዎቸ ወደ ኢትዮጵያ ማተኮርና የማስታወቂያ ገደብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:25:55 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG