ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ የመልካም አስተዳደር ይዞታ ዙሪያ ያደረገውን ዘርፈ ብዙ የጥናት ውጤት በቅርቡ ይፋ አድርጓል።
ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ ደረጃ በሚገኙ የመንግስት አስተዳደር ዘርፎች የመልካም አስተዳደር ጉድለት በስፋት መታየቱን ጥናቱ ያመለከተው።
በተለይ በፍትሕ ዘርፍ ታዩ የተባሉትን በዜጎች በእኩል የመዳኘት መብት ጉድለቶች የሚዳስስ የአንድ የሕግ ባለ ሞያ ትንታኔ ከዚህ ይከታተሉ።
ዶ/ር ፍጹም አቻም የለህ በዚህ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው በጥብቅና ሞያ የተሰማሩት የሕግ ባለ ሞያ ናቸው።
ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።