በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአስመራ ከተማ በዩኔስኮ ለመመዝገብ እጩ ሆነች


Asmara city
Asmara city

ከዛሬ 700 አመት ገደማ በፊት ገዛ ግረቶም፣ ገዛ ሺለሌ፣ ገዛ ሰረንሰር እና ገዛ አስሜ የተባሉ በአራት የተከፈሉ ሰፊ የቤተሰብ አባላት በአስመራ ከተማ ይኖሩ ነበር። የዛሬዋ አስመራ በዛን ዘመን የንግድ መተላለፊያ ቦታ ነበረች። ታዲያ በዛን ጊዜ በአራቱ የቤተሰብ አባላት መካከል ስምምነት ይጠፋል በዚህም ምክንያት ከተማዋ ሰላም ይርቃታል። ለችግሩ መፍትሄ ይሆን ዘንድ የአራቱ ቤተሰብ አባላት ሴቶች ይሰባሰቡና ሰላምን እንዴት እንድሚያሰፍኑ መከሩ እናም የሰላም ህግጋትን አወጡ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አስመራ ሰላም ሆነች፣ የከተማዋ መጠሪያም የሴቶቹን በጎ ተግባር ለማወደስ አስመራ ተባለ። አስመራ ማለት በትግሪኛ ሴቶቹ አሰመሩ እንደማለት ነው።

የአስመራ ከተማ የኤርትራ ዋና ከተማ ተብላ የተሰየመችው እ.አ.አ 1897 በጣልያን ቅኝ ግዛት በነበረችበት ወቅት ነው። አስመራ የምትታወቀው በከተማዋ ውበት በተለይም በማስተር ፕላኗ ሲሆን በከተማዋ የሚገኙት ታሪካዊ ሕንፃዎች ከአፍሪካ ከተሞች የተለየች ያደርጋታል።

ይህ ልዩነቷ አስመራን በዩኔስኮ UNESCO የአለም ታሪካዊ ስፍራዎች ወይም “World Heritage”፤ በ19ኛው ክፍለዘመን ማብቂያና በሀያኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ የተገነቡ ህንጻዎቿን፤ ታሪኳን እና የግንባታ ውበቷን ሊመዘግብ እጩ አድርጓታል።

ነዋሪነቱ በዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ኢሳያስ ተስፋማሪያም አሁን ካሊፎርኒያ በሚገኘው በሁቨር የጥናት ማእከል የቤተ መዛግብት ባለሙያ ሆኖ ይሰራል፤ እንዲሁም በስታንፎርድ ዪኒቨርሲቲ በታሪክና በቋንቋ መምህርነት በመስራት ላይ ይገኛል።

Issayas Tesfamariyam
Issayas Tesfamariyam

ከኢሳያስ ተስፋማሪያም ጋር ስለአስመራ ከተማ የተደረገ ጨዋታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:28 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG