በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማኅበራዊ ሚዲያ እና ኢትዮጵያውያን


በእውቀቱ ስዩም፣ አምለሰት ሙጬ እና ሳያት ደምሴ
በእውቀቱ ስዩም፣ አምለሰት ሙጬ እና ሳያት ደምሴ

ኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ሚዲያን እንዴት ይጠቀሙበታል? እንዲሁም ታዋቂ ኢትዮጵውያን እና የማያውቁት የፌስቡክ ገጾቻቸው በሚል ርእስ ጽዮን ግርማ ውይይት አዘጋጅታለች፡፡ እንዳልካቸው ኀይለ ሚካኤል፣ የትነበርክ ታደለ፣በእውቀቱ ስዩም ፣ ሳያት ደምሴ፣ አምለሰት ሙጬ እና ኤልሻዳይ ነጋሽ በዚህ ዘገባ ተካተዋል፡፡

እንዳልካቸው ኀይለ ሚካኤል ይባላል ትምህርትን በኢንተርኔት ስለ ማቅረብ (E-learning) አስመልክቶ ጥናት አድርጓል፡፡ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምሕር ነበር፡፡ የዞን ዘጠኝ የጡመራ መድረክ አንዱ መስራች ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካን አገር በሚገኝ ኦሪገን ዩቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ጥናቱን እያደረገ ነው፡፡

የትነበርክ ታደለ በመምሕርነትና በትምሕርት አስተዳደር ሥራ ላይ ረዘም ላሉ ዓመታት አገልግሏል፡፡ በማኅራዊ ሚዲያ ዘርፍ በዋነኝነት ተጠቃሽ የኾነውን ፌስቡክን ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ እንደዋነኛ የብዙሃን መገናኛ መድረክነት ይጠቀምበታል፡፡ ይጽፋል፣ ይወያያል፡፡ ጽዮን ግርማ ኢትዮጵያውያን እና የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ ሁለቱንም እንግዶች አወያይታ የሚከተለውን ዘግባለች፡፡

እንዳልካቸው ኀይለሚካኤልና የትነበርክ ታደለ
እንዳልካቸው ኀይለሚካኤልና የትነበርክ ታደለ

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ማኅበራዊ ሚዲያ እና ኢትዮጵያውያን(አንድ)
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የፌስቡክና ትዊተር ገጾች ለአርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች ዐይነተኛ የመገናኛ መድረኮቻቸው ናቸው፡፡ ድርስ ሥራዎችና የመድረክ ዝግጅቶች ሲኖሯቸው ያስተዋውቁባቸዋል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች የመልካም ምኞት መግለጫዎቻቸውን ያስተላለፉበታል፡፡ በጉዳዮች ላይ ሐሳብ ሲኖራቸው አስተያየታቸውን ያሰፍሩበታል፡፡ ማኅበራዊ ድረ ገፆችን በዚህ መንገድ የሚጠቀሙበት ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ጥቂት ናቸው፡፡

በምትኩ ያለአርቲስቶቹ ዕውቅናና ፈቃድ ማንነታቸው የማይታወቅ ሰዎች ስማቸውንና ምስለ ገፃቸውን እየተጠቀሙ የሚያንቀሳቅሷቸው የፌስቡክ ገጽ ባለቤቶች ቁጥር ከፍ ያለውን ቁጥር ይይዛል፡፡ ጽዮን ግርማ ከእነዚህ አርቲስቶች መካከል ጥቂቶቹን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አሠናድታለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ማኅበራዊ ሚዲያ እና ኢትዮጵያውያን(ሁለት)
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኤልሻዳይ ነጋሽ ከጋዜጠኝት፣ከቴክኖሎጂ እና ከሚዲያ ግንኙነት ጋራ በተያያዘ የዳበረ ዕውቀትና ክህሎት ባለቤት ነው፡፡ አሁን በዲጂታል ሚዲያ የማኔጅመንት ሥራ ይሠራል፡፡“ኢትዮጵያውያን ማሕበራዊ ሚዲያን እንዴት ይጠቀሙበታል?” ለሚለው የመወያያ ጉዳይ ማሳርጊያ እንግዳ ነው፡፡

ኤልሻዳይ ነጋሽ
ኤልሻዳይ ነጋሽ

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ማኅበራዊ ሚዲያ እና ኢትዮጵያውያን (ሦስት)
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG