በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ከጥራት ይልቅ ሽፋን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው” ባለሞያዎች


በኢትዮጵያ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ
በኢትዮጵያ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ

"የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ሽፋንና ጥራት በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ምን ይመስላል?" በሚል መነሻ ሐሳብ ይህ ዘገባ በአማራ፣በአፋር እና በኦሮሚያ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት መምሕራንን ስለ ትምሕርት ጥራቱ ይጠይቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ያጠናው ጥናት በዘገባው ተካቷል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምሕርት በበቂ ሁኔታ መዳረሱን፤ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ያልተከፈተበት መንደር ፈልጎ ለማግኘት አስቸጋሪ መኾኑን፤ ይህን በተመለከተ ጥናት ያጠኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ የትምሕርት ሚኒስቴር እና ሌሎች በኢትዮጵያ የትምሕርት ጉዳይ ላይ ሪፖርት የሚያወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማት፤የኢትዮጵያ መንግሥት ካስመዘገባቸው ስኬቶች አንዱ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርትን ለሁሉም ማዳረስ መቻሉ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ጥራቱስ?

ትምሕርት ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም ዕድሜያቸው ከሰባት እስከ ዐስራ አራት ከሚደርስ ታዳጊዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት መጀመሪያ ደረጃ የትምሕርት ዕድል አግኝተዋል፡፡ እንዲሁም ትምሕርት ቤት ለመግባት ትክክለኛ ዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ዕድሜያቸው ሰባት ዓመት ከሆናቸው ታዳጊዎች ውስት 86 በመቶ የሚኾኑት ትምሕርት ቤት የመግባት ዕድል አግኝተዋል፡፡

በሌላ በኩል ሌሎች ምሑራን እና የኢትዮጵያ የትምሕርት ጥራት ጉዳይ ሲነሳ አስተያየታቸውን የሚሰጡ አካላት በኢትዮጵያ ትምሕርት በቁጥር ደረጃ ቢዳረስም ጥራቱ ግን አጠያያቂ እንደኾነ ይናገራሉ፡፡

በተለይ አብዛኛውን የሕብረተሰብ ክፍል በሚይዘው የገጠሪቱ አትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች አንድ ትምሕርት ቤት ማሟላት ሚገባው መሠረታው ነገር እንዳልተሟላ፣ወላጆችም በትምሕርት ላይ ምንም ተስፋ ስለሌላቸው ተማሪዎች በአግባቡ ትምሕርታቸውን እንደማይከታተሉ ይነገራል፡፡ይህን ጉዳይ በተመለከተ አለምነሽ አሌ የተባለች በደቡብ እና ሰሜን ጎንደር ሁለት የተለያዩ ትምሕርት ቤቶች የማስተማር ልምድ ያላት መምሕርት ትናገራለች፡፡

ተመሳሳይ ችግር እንዳለበት የሚነገረው አፋር ክልል ነው፡፡አብዛኞቹ የአፋር ክልል ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ አርብቶ አደር በመኾናቸው፤ አካባቢው በቀላሉ በድርቅ የሚጠቃ በመኾኑ ፣ አብዛኛውን ጊዜ ረሃብ በማስተናገዳቸውና በተለያዩ ምክንያቶች በዛ አካባቢ ያለው የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ጥራት ሁሌም ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡

በአፋር ክልል አሳይታ ከተማ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለማስረዳት መምሕር መሐመድ ኡመርን በዚህ ዘገባ ተካቷል፡፡ ወ/ት ፋሲካ ሙሉጌታም በኦሮሚያ ክልል ኢንጪኒ በተባለች ከተማ በሚገኝ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት መምሕር ናት፡፡ ልምዷን ትናገራለች፡፡

ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ
ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ

ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡ አካዳሚው የአንደኛ ደረጃ ትምሕርትን አስመልክቶ ስላጠናው ጥናት ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ እናንተ አድማጮቻችን በማሕበራዊ ሚዲያ ፌስ ቡክ ላይ ይህንኑ የውይይት ርእስ አስመልክቶ የሰጣችኋቸው አስተያየቶችም ተካተዋል፡፡ ሁሉንም እንግዶች አነጋግራ ፕሮግራሙን የሠራችው ጽዮን ግርማ ነች፡፡

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

የፌስ ቡክ ተሳታፊዎች የሰጣችሁት አስተያየትም ተካቷል።

“የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ከጥራት ይልቅ ሽፋን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው”ባለሞያዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:27:09 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG