በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ ስደተኞች በአውሮፓ ባሕር


ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገሮች የመጡ ወደ 900 የሚሆኑ ፍልሰተኞችና ስደተኞች፣ በደቡብ ጣልያን የተባበሩት የአውሮፓ የባሕር ሃይሎች ከመስመጥ አድነዋቸዋል።

ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገሮች የመጡ ወደ 900 የሚሆኑ ፍልሰተኞችና ስደተኞች፣ በደቡብ ጣልያን የተባበሩት የአውሮፓ የባሕር ሃይሎች ከመስመጥ አድነዋቸዋል።

ትናንት ማክሰኞ 900 የሚሆኑ በሕይወት የተረፉ ሲሆን ባጠቃላይ ባለፈው የሳምንት ማብቂያ ላይ አንድ ሺህ የሚሆኑ ፍልሰተኞች ከሜዲትራንያ ባሕር ላይ ማዳን ተችሏል።

ዛሬ ማለዳ 239 የሚሆኑ ኤርትራውያን ከመሲና ባሕር ዳር በኖርዌይ መርከብ “ስየም ጲሎት”(Siem Pilot) ተብሎ በሚጠራው መርከብ ተሳፍረዋል። ከሰዓት በኋላ ደግሞ ከ650 በላይ የሚሆኑ ፍልሰተኞች በብሪታንያ የባሕር ሃይል መርከብ ኢንተርፕራይዝ ተሳፍረው ፣በደቡብ ኢጣልያ ተሻግረው ወደ ካቲና ባሕር ዳር ገብተዋል። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ኤርትራውያን መሆናቸው ታውቋል።

የአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኞች በቦታው ተገኝተው እንደዘገቡት፤ ከሊቢያ ባሕር ዳር ተነስተው መንገድ የጀመሩት ፍልሰተኞችና ስደተኞች የጭንቀት ጥሪ ወደ ጣልያን ከላኩ በኋላ የጣልያን አስተዳዳሪዎች እንዳተረፏቸው፤ አብዛኞቹ ወንዶች ሲሆኑ ከመካከላቸው ደግሞ ሴቶችና ሕጻናት እንደሚገኙ የአውሮፓ መሪዎች ገልጸዋል።

የጣልያን ቀይ መስቀል፣የሕጻናት አድን ድርጅት(Safe the Children)እና የተለያዩ ርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች በቦታው ተገኝተው የተረፉትን ስደተኞች ጤንነት በማረጋገጥ መዝግበው በአውቶብስ አሳፍረዋቸዋል።

የኖርዌይ መርከብ ውስጥ እንዲገቡ ፍቃድ የተሰጣቸው የአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኞች እንደዘገቡት ፍልሰተኞቹ ተዳክመው እንደነበር ገልጸዋል። ነገር ግን፣ በሰላም ወደ አውሮፓ መሬት በመግባታቸው ደስተኞች እንደሆኑ ተናግረዋል።

በዚህ ዓመት ብቻ የተባበሩት አውሮፓ መንግስታት ድርጅት ሃይሎች እስካሁን ድረስ ወደ 100 ሺህ የሚሆኑ ፍልሰተኞች ከሜዲትረናንያ ባሕር በሕይወት እንደተረፉ አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG