በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በመላው አፍሪካ ላሉ ሕፃናት አሁንም ከፍተኛ እርዳታ ያስፈልጋል" አምበር ስታይም


ከአምበር ስታይም ጋር የተደረገ አጭር ቆይታ
ከአምበር ስታይም ጋር የተደረገ አጭር ቆይታ

ወደ አሜሪካ በማደጎ የመጣችው እ.አ.አ በ1970 ነው። ለስራ ወደ ኢትዮጵያ በመጡ አሜሪካውያን። ያኔ የስምንት አመት ልጅ ነበረች።

አምበር ስታይም የተወለደችው በጎንደር ደብረታቦር ከተማ ነው። የ3 አመት ልጅ እያለች ከመሬት መጫወቻ መስሏት ያነሳችው ቦንብ ፈንድቶ ሁለት እጆቿን አሳጥቷታል። በዚህ ምክንያት የተለየ አርዳታ ፈላጊ ሆነች። ኢትዮጵያ በሚገኘው የክርስቲያን የህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ከኖረች በኃላ ለስራ ኢትዮጵያ ይኖሩ ከነበሩት ከአሜሪካውያኑ የማደጎ ወላጆቿ ጋር ወደ አሜሪካ መጣች።

የመጀመሪያ ዲግሪዋን በማህበራዊ ጉዳይ አጠናቃ ለተወሰነ አመት በሙያዋ ካገለገለች በኃላ የከፍተኛ ትምህርቷን በመቀጠል በማህበራዊ ጉዳይ ሙያ አጠናቃለች። "እናም ትምህርቴን ስጨርስ በሲያትል ለሚገኙ በጎዳና የሚኖሩ ህፃናትና ሴቶችን በመርዳት ስራዬን ጀመርኩ" ትለናለች አምበር ስታይም።

"በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ከፍተኛ እርዳታ አሁንም ያስፈልገናል፡ በረሃብ በበሽታና በተፈጥሮ መዛባት ምክንያት ብዙ ሕጻናትና ሴቶች እርዳታ ይፈልጋሉ።"

በማደጎ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡ አዳጊ ኢትዮጵያውያን ዋነኛው ችግር ሊኖሩበት ስለመጡበት ሃገር ትክክለኛ መረጃን አለማግኘት ሲሆን የልጆቹን ደህንነት የሚከታተል አለመኖሩም ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው። አምበር እንዳለችው የኢትዮጵያ መንግስት ወይም የሚመለከተው አካል በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ መስራት ይገባዋል።

ኢትዮጵያውያን የማደጎ ልጆች በአሜሪካን ሃገር
ኢትዮጵያውያን የማደጎ ልጆች በአሜሪካን ሃገር

"በመላው አፍሪካ ላሉ ሕፃናት አሁንም ከፍተኛ እርዳታ ያስፈልጋል" አምበር ስታይም
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG