ሄዘር ማክስዌል አሜሪካዊት የጃዝ ሙዚቃ ድምፃዊና አለም አቀፍ የባህል ሙዚቃ አጥኚ ናት። በVOA በአፍሪካ የሬድዮ ፕሮግራም “Music Time in Africa” ሙዚክ ታይም ኢን አፍሪካ በተሰኘው የሬድዮ እና የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ በማዘጋጀትም ትታወቃለች።
“Young Ethio-jazz Band” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ተወልደው ያደጉት በዩናይትድ ስቴትስ ኦክላንድ ካሊፎርኒያ ነው። እድሜያቸው ከዐስራ ሦስት እስከ ዐስራ ስምንት የሆኑት አነዚህ ወጣቶች በጋራ ሙዚቃን መጫወት የጀመሩት የዛሬ አራት ዓመት ነው።"ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ" ይላል ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ።
ደራሲ እና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት የሚጻፉ አንዳንድ መጽሐፎች በሕብረተሰብ መካከል፣ በተለይ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር የሚያላሉ፣አልፎ አልፎ ደግሞ እንዲበጠስ የሚያግዙ አስተያየቶችን እና ሐሳቦችን አያለሁ፡፡”ይላል፡፡
የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉ ያስከተለው ተቃውሞን ተከትሎ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - ኦሕዴድ ዕቅዱን መሠረዙ ይታወቃል፡፡በርካታ አድማጮች በዕቅዱና ዕቅዱን ተከትሎ በተነሣው ተቃውሞ ዙሪያ ጥያቄዎች ልከውልናል፡፡የጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን ሁለት ምሑራን ጋብዟል፡፡
ኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ሚዲያን እንዴት ይጠቀሙበታል? እንዲሁም ታዋቂ ኢትዮጵውያን እና የማያውቁት የፌስቡክ ገጾቻቸው በሚል ርእስ ጽዮን ግርማ ውይይት አዘጋጅታለች፡፡ እንዳልካቸው ኀይለ ሚካኤል፣ የትነበርክ ታደለ፣በእውቀቱ ስዩም ፣ ሳያት ደምሴ፣ አምለሰት ሙጬ እና ኤልሻዳይ ነጋሽ በዚህ ዘገባ ተካተዋል፡፡
"ይህን መንግሥት ከሌሎቸ መንግሥታት ለየት የሚያደርገው፤ ‘እኔ ይህን ያሕል ሞተብኝ’ ብሎ ከተሰላፊዎቹ እኩል ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባል" ከሕግ ባለሞያ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር የተደረገ ቃል ምልልስ (ክፍል ሁለት)
አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።የሕግ አስተማሪና ተመራማሪም ናቸው። በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በድጋሚ ስላገርሸው ተቃውሞ እና የመንግሥት ምላሽ፤ ከሕግ አኳያ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡
“ሃብት ያለው ሰው አይታሰርም። ተፈርዶባቸው እስር ቤት ያሉ ባለ ሃብት መንገድ ላይ ሲሄዱ ሌላ ሰው ገጭተው ሌላ ክስ ተመሠረተባቸው። አቃቤ ሕግ ምሥክር ማስፈራራት የሃሰት መረጃ ማስጠናት። በጥናቱ ካገኘናቸው ውስጥ ናቸው።” አቶ ተካ ገብረ የሱስ፤ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዲሬክተር።
ዶ/ር ፍቅሩ ማሩና ሌሎችም ከሙስና ጋር በተያያዙ ክሦች እሥር ቤት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ጉዳይ ለፊታችን ማክሰኞ፤ ጥቅምት 9/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡ ጠበቆቻቸው ደንበኛቸው የተከሰሱበት መዝገብ አብረዋቸው ከተከሰሱት ሰዎች ጉዳይ ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ ተነጥሎ እንዲወጣና እንዲታይ እየጠየቁ ነው፡፡
Dr. Fikru Maru's Case in Ethiopia - 10-17-15 /mp3 audio: length 30'16" size 27.7mb/
ዶ/ር አምባዬ ወልደ ሚካኤል የማሕጸንና ጽንስ ባለሞያ ናቸው፡፡ሥራ በጀመሩበት አዲስ አበባ ፌስቱላ ሆስፒታል ዐስራ አራት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በዚህ ቆይታቸው በሞያቸው ከሚያገለግሏቸው ሴቶች በተጫማሪ በሆስፒታሉ ውስጥ አንድ ቡድን በማዋቀር ከአዲስ አበባ ውጪ በሦስት ቦታዎች የፌስቱላ ሕክምና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ማዕከላትን አቋቁመዋል፡፡
ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገሮች የመጡ ወደ 900 የሚሆኑ ፍልሰተኞችና ስደተኞች፣ በደቡብ ጣልያን የተባበሩት የአውሮፓ የባሕር ሃይሎች ከመስመጥ አድነዋቸዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጅያ ድርጅትከፍተኛ ኮሚሺነር አንቶንዮ ጉቴረስ በግጭት ምክንያትና የሚደርስባቸዉን ግፍ ሸሽተዉ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እጅግ መጨመር፣ የተራድኦ ድርጅቶች በገንዘብ እጥረት እጃቸዉ ታሶሮ እርዳታ ሊያቀርቡ ያልቻሉበት ጊዜ ጋር መገጣጠሙን በመጥቀስ አስጠነቀቁ።
“ይህ ቀውስ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ እልቂትና ፍልሰት ነው።” ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን
አቡነ ፍራንሲዝ ሊቀ-ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን ከዩናይትድ ስቴትሷ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው አንድሩስ የአየር ኃይል መደብ ዛሬ፤ ማክሰኞ መስከረም 11/2008 ዓ.ም ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ምክትላቸው ጆ ባይደን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ከሦስት እስከ አምስት ዓመታት ጠፈር ላይ የራሷ ሳተላይቶች ሊኖሯት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የኅዋ ሳይንስ ማኅበር የበላይ ጠባቂ አቶ ተፈራ ዋልዋ አስታውቀዋል፡፡
Ethiopia may soon launch a satellite - Teferra Walwa
ባለፈው ሣምንት አርብ ነሐሴ ዘጠኝ ቀን 2007 ዓ.ም በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን መሐንዲሶችና ሳይንቲስቶች ማኅበር፣የካሪቢያን አዕምሮ ጥበቃ ማኅበር እንዲሁም የኢትዮ-ጵያ ወጣት ባለሞያዎች ማኅበር በጋራ በመኾን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የዪናይትድ ስቴትስ የአዕምሮአዊ ፈጠራ ውጤቶችና የንግድ ምልክቶች ኤጀንሲ መሥሪያ ቤት ጋር በመተባበር አንድ ጉባኤ አዘጋጅተው ነበር፡፡
“ችግሩ እራሣቸው የዘሩት ፍሬ ነው” ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
በሚሌ ወረዳ የሀርሲስ ቀበሌ ነዋሪዎች በድርቅ መጎዳታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ግርማይ ጋብሩ በአፋር ክልል ታዘዋውሮ ዘግቧል።
ተጨማሪ ይጫኑ