በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዳጊ ወጣት የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋቾች-በካሊፎርኒያ


 Young Ethio-jazz ባንድ አባላት
Young Ethio-jazz ባንድ አባላት

ኢትዮጵያዊ ዜማዎችን በተለያዩ መድረኮች በመጫወት ለውጭው አድማጭ ኢትዮጵያዊነታቸውና ባህላቸውን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ። በተለይም የኢትዮ-ጃዝ የሙዚቃ ስልት የሆነውን የዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ ሙዚቃዎችን በመድረክ በመጫወት ይታወቃሉ።

'Young Etho-jazz band' ያንግ ኢትዮ-ጃዝ ባንድ የተመሰረተው በአዳጊዎቹ ወላጆች የጠነከረ ጓደኝነትና ኢትዮጵያዊነትን ለልጆቻቸው ለማስተላለፍ ካላቸው ፍላጎት ነበር። ከሙዚቃ ባንድ አባላቱ የአንዱ ልጅ አባት የሆነው አቶ ሲራክ ተግባሩ በተለየ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለወጣቶቹ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል።

አቶ ሲራክ ተግባሩ የሙዚቃ አሰልጣኝ
አቶ ሲራክ ተግባሩ የሙዚቃ አሰልጣኝ

የሳክስፎን የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች የሆነው አቶ ሲራክ ልጆቹን በማሰባሰብና በመኖሪያ ቤቱ የሙዚቃ ልምምድ እንዲያደርጉበት ከማዘጋጀት ጀምሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ፣ አጠቃላይ የሙዚቃን ህግና የሙዚቃ መሳሪያውን በማስተማር ላይ ይገኛል። በቅርቡም ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴት አዳጊ ወጣቶችን በማሰባሰብ የኢትዮጵያን ሙዚቃ የማስተማር እቅድ አለው።

“መሆን የምትመኙትን ለመሆን ጣሩ፤ ራሳችሁን ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ።” ዮሃንስ ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ የተናገረው ነው።

መስታወት አራጋው የሙዚቃ ባንድ አባላቱን አነጋግራቸዋለች።

ሙሉ ዝግጅቱን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ።

አዳጊ ወጣት የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋቾች-በካሊፎርኒያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG