በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የሞያ ማማከር የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ነው 👉. በሌላ በኩል ደግሞ በሕክምናና በማያቋርጥ አገልግሎት መስጫ ውስጥ ስለሚሠሩ ተጎጂዎችም ናቸው (ዝርዝሩን ከቃለ ምልልሱ ይከታተሉ)
"በኮሮናቫይረስ ተይዞ ሕይወቱ ያለፈው ባለቤቴን አስክሬን ሳልቀብር እኔ መያዜን ነገሩኝ። ሕፃናት ልጆች እቤት ውስጥ አሉኝ፤ ልጆቼን ጥያቸው እንዳልሄድ እኔም ስጋት ላይ ነኝ" ይላሉ በላስ ቬጋስ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አበራሸ ኦሮሞ የተባሉ የሦስት ልጆች እናት። "ባለቤቴ ልጆቼ ፊት ነው ትንፋሽ አጥሮት ሕይወቱ ያለፈው ፤ ቤተሰቤን ከባድ መከራ ውስጥ የከተተ ሐዘን አድርሶብኛል" ብለውናል ።
በጎንደር ከተማ ሁለት በሕገወጥ መንገድ የተደራጀ ካምፕ ተገኝቷል ተብሏል አንድ የቴሌ ሠራተኛ ”ሦስት ሆነን ታግተን በገንዘብ ነው የተለቀቅነው" ብሏል
👉 በጣሊያን ሚላን ከተማ የሚገኙት የ15 ዓመቷ ግሎሪያእና የ14 ዓመቷ ከንአን በኮረናቫይረስ ምክኒያት እናታቸው ወሮ ሃና ገዛኢ በሆስፒታል አባታቸው አቶ ነጋሲ ክብሮም ደግሞ በአንድ ክፍል በር ዘግተው ይገኛሉ። "ለወላጆቻችን እየፀለይን ነው" ይላሉ ። 👉በስካይፕ የተደረገውን ውይይት ተከታተሉት
በቸልተኝነት ምክኒያት እኔ ባመጣሁት ኮረናቫይረስ በኩላሊት እጥበት ሕክምና ላይ የነበረችውን ባለቤቴን ወሮ ሃና ገዛኢን ላሲዛት ችያለሁ ሲሉ አቶ ነጋሲ ክብሮም የተባሉ በጣሊያን ሚላን ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። አቶ ክብሮም የሕንፃ እቃዎች መሸጫ ባለቤት በመሆናቸው ሱቃቸውን ከፍተው ሲሸጡ እንደነበር ገልፀው ቀን ከገበያተኛ የተላለፈባቸው ኮረናቫይረስ ማታ ቤት ሲገቡ ደግሞ ባለቤታቸውን ማስያዛቸውን ገልፀውልናል።
ምንም ዓይነት የሕመም ስሜትም ሆነ ምልክት ሳይኖርባቸው በኮረናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ወ/ሮ ሳራ ሚካኤልየተባሉ በጣሊያን ሚላን ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊት ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ ያለበት ማነው?
ብልፅግና ፓርቲ በወረዳና በቀበሌዎች ውስጥ ሳይቀር አባላቱ ስብሰባ እንዲያካሂዱ እያደረገ ነውበሚል ወቀሳ እየቀረበበት ነው።
በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስልክና ኢንተርኔትስለተቋረጠባቸው ኮረና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችላቸውን መረጃ ከሌሎች ኢትዮጵያውያንእኩል እንዳያገኙ ተደርገዋል ሲል ሂዩማን ራይትስ ወች የኢትዮጵያ መንግስትን ወቀሰ።
ለኮረና ቫይረስ ተጋልጠው ይሆናል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎች የሚወሰደው ናሙና እንዴት ይመረመራል? ውጤቱን ለማወቅስ ስንት ቀን ይወስዳል?
ለኮረና ቫይረስ ተጋልጠዋል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችን ነጥሎ ማቆያ ጣቢያዎች ይዘት ምን ይመስላል? ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለሞያ ጠይቀን ያጠናቀርነውን ዘገባ ተከታተሉ።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ ከ20 ዓመት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ በቆየ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን አጥቢያ ላይ የደቦ ጥቃት መድረሱን እና ሦስት ምዕመናን መጎዳታቸውን የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቤ ይልማ ዋቄ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። በጥቃቱም ቤተእምነቱ ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን ገልፀዋል።
ስድስተኛው የ2012 ዓ.ም ሃገር አቀፍ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሆን ቀጠሮ ተቆርጧል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ፣ ተአማኒና ውጤቱም ተቀባይነት የሚኖረው እንዲሆን ለማድረግ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር ተባብሮ ለመሥራት እየተጋ መሆኑን ይናገራል። በሌላ በኩል ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤታቸው ከወዲሁ እያቀረቡ ነው።
“ጉዳዩ በሕጉ መሠረት እልባት እንዲያገኝ እናደርጋለን” – ኦፌኮ
“ሰብዓዊ መብትትን የሚጥሱ ሰዎች ላይ ለምን እርምጃ ተወሰደ? የሚል ተቃውሞ ማሰማት እጅግ አሳዛኝ ነው” - አቶ ታዬ ደንዳአ
የአቶ ጃዋር መሐመድን የዜግነት ጉዳይ በተመለከተ ምርጫ ቦርድ በሰጣቸው ቀነ ገደብ መሠረት ምላሽ እንደሚሰጡ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ገለፁ።
ከአንድ ወር ተኩል በፊት ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት ሸሽተው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ እያሉ “በታጣቂዎች ታገቱ” ከተባሉ ከዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ውስጥ ሃያ አንዱ መለቀቃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ይፋ ቢደረግም ልጆቻቸው የታገቱባቸው ቤተሰቦች ግን እስካሁን ምንም የሰሙት ነገር አለመኖሩን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ከአንድ ወር ተኩል በፊት ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት ሸሽተው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ እያሉ “በታጣቂዎች ታገቱ” ከተባሉ ተማሪዎች ውስጥ የተወሰኑት ወላጆች ፤ ልጆቻቸው ከታገቱ ጀምሮ መፍትሔ ለማግኘት ያህል በመንከራተት ላይ እንዳሉ ገልፀው ስለመለቀቃቸውም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ