ዋሽንግተን ዲሲ —
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ውስጥ በሁለት መኖሪያ ቤት ከባድ መሳሪያ ጭምር ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ላይ መንግሥት እርምጃ በወሰደበት ጊዜ አንድ ነጋዴና አንድ ሹፌር በአጠቃላይ ሁለት ሰዎችከታገቱበት መለቀቃቸውን የጎንደር ከተማ ከንቲባ አስታወቁ።
በተጨማሪም ቡድኑ አራት የፀጥታ አባላትንና ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉን እንዲሁም አራት ሰዎች መቁሰላቸውን አያይዘው ገልፀዋል። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አንዳንድ ሰዎች መንግሥት በዚህ አሳቦ “በፋኖስም የተደራጁ ሰላማዊ ወጣቶችን ለማጥፋት ነው” የሚል ሐሳብ ቢሰነዝሩም ሌሎች ደግሞ “የለም በከተማው ነዋሪዎችን በተለይ ነጋዴዎች እና ገንዘብ አላቸው ብለው ያሰቡትን ሰዎች የሚያስጨንቁ” ናቸው በሚልአስተያየት ሰጥተዋል። እንደውም መንግሥት እርምጃ ሳይወስድ ዘግይቷል የሚሉም አሉ።
በሌላ በኩል “ሳንጃ” በሚባል አካባቢ ከታገቱ በኋላ ቤተሰቦቻቸው በከፈሉት 500 ሺህ ብር መለቀቃቸውን ከገለፁ ሦስት የኢትዮ - ቴሌኮም ሠራተኞች አንዱን አነጋግረናል።
(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ