በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብልፅግና ፓርቲ ስብሰባና የሚቀርብበት ወቀሳ


PP party
PP party

ብልፅግና ፓርቲ በወረዳና በቀበሌዎች ውስጥ ሳይቀር አባላቱ ስብሰባ እንዲያካሂዱ እያደረገ ነውበሚል ወቀሳ እየቀረበበት ነው።

የፓርቲውን ሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ በጉዳዮ ላይ ከአሜሪካ ድምጽተጠይቀው፤ “ስብሰባዎቹ የተደረጉት የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መደረግ ስለሚገባውጥንቃቄ ለመነጋገርና አንድ ዓይነት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው’’ ብለዋል። “የኢንተርኔትመጨናነቅና ገጠር አካባቢ ደግሞ ከስብሰባ ውጪ የመገኛ አማራጭ ስለሌለ የተካሄዱ ናቸው’’ብለዋል።

በተጨማሪም “የብልፅግና ስብሰባ ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቱ በተለያየ ቦታ ሰዎች በጣምተጠጋግተውና ተፋፍነው እየታዩ በመሆኑ መንግስት በምንድነው የሚይስቆመው?” በሚልለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ከደህንነት ዘርፍ ኃላፊዎች ጋርባደረጉት ውይይት ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን አንስቶ፣ የደህንነት ዘርፉ በቁጥር የበዛ ሰውየሚሳተፍባቸውን ስብሰባዎች የሚያስቆም እና ማሕበራዊ ርቀትን መጠበቅን እንደሚያስተገብር ተገልጿል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የብልፅግና ፓርቲ ስብሰባና የሚቀርብበት ወቀሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:51 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG