የብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንዳ በበኩላቸው “የኦነግ ሸኔ በሚል የሚጠራው የታጠቀ ቡድን ስልክና ኢንተርኔትን በመጠቀም ባደራጃቸው የትስስር ሰንሰለት በሕዝብ ላይ እጅግ ዘግናኝ ድርጊቶችን ሲፈፅም መቆየቱን ገልፀው፤ ይህ ሰንሰለት ከላይ እስከ ታች የተቋረጠባቸውና ቡድኑ የተዳከመባቸው ኃይሎች በኮረና ቫይረስ አሳበው ኢንተርኔቱን በጩኸት ለማስመለስ የያዙት ጥረት ነው “ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ስለ ኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስፈልገውን መረጃ መንግስት በራዲዮ፣በቴሌቭዥን እና በጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች አማካኝነት ለኅብረተሰቡ እንዲደርስ እያደረገ ነው ብለዋል። የሂዩማንራይትስ ወች የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪ ላቲሺያ ባይደር ዜጎችን ከጥቃት የመከላከልም ሆነ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ የመንግስት ግዴታ ነው ብለዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
ረቡዕ መጋቢት 25, 2020 ተላልፎ የነበረውን መሰናዶም ማስፈንጠሪያውን በመጫን
ማዳመጥ ይቻላል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ