በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ባለቤቴ ሆስፒታል በአክስጅን ፤ እኔ ደግሞ ቤት ውስጥ ተነጥዬ ተቀምጫለሁ"- በኮረናቫይረስ የተያዙ ባለትዳሮች


በቸልተኝነት ምክኒያት እኔ ባመጣሁት ኮረናቫይረስ በኩላሊት እጥበት ሕክምና ላይ የነበረችውን ባለቤቴን ወሮ ሃና ገዛኢን ላሲዛት ችያለሁ ሲሉ አቶ ነጋሲ ክብሮም የተባሉ በጣሊያን ሚላን ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። አቶ ክብሮም የሕንፃ እቃዎች መሸጫ ባለቤት በመሆናቸው ሱቃቸውን ከፍተው ሲሸጡ እንደነበር ገልፀው ቀን ከገበያተኛ የተላለፈባቸው ኮረናቫይረስ ማታ ቤት ሲገቡ ደግሞ ባለቤታቸውን ማስያዛቸውን ገልፀውልናል።

ባለቤታቸው ሕመሙ ስለጠናባቸው በሆስፒታል መተንፈሻ ተገጥሞላቸው መተኛታቸውንና እርሳቸው ደግሞ እቤትውስጥ ከልጆቻቸው ተነጥለው በአንድ ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። አቶ ነጋሲ ሰዎች ከቸልተኝነት ስሜትወጥተው ራሳቸውን በሚገባ እንዲከላከሉ መክረዋል። ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘገባ አሰናድታለች።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

"ባለቤቴ ሆስፒታል በአክስጅን ፤ እኔ ደግሞ ቤት ውስጥ ተነጥዬ ተቀምጫለሁ"- በኮረናቫይረስ የተያዙ ባለትዳሮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:32 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG