በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የባለቤቴን አስክሬን ሳልቀብር እኔም በኮሮናቫይረስ መያዜ ተነገረኝ " - የሦስት ልጆች እናት ወ/ሮ አበራሽ ኦሮሞ


"የባለቤቴን አስክሬን ሳልቀብር እኔም በኮሮናቫይረስ መያዜ ተነገረኝ "
"የባለቤቴን አስክሬን ሳልቀብር እኔም በኮሮናቫይረስ መያዜ ተነገረኝ "

"በኮሮናቫይረስ ተይዞ ሕይወቱ ያለፈው ባለቤቴን አስክሬን ሳልቀብር እኔ መያዜን ነገሩኝ። ሕፃናት ልጆች እቤት ውስጥ አሉኝ፤ ልጆቼን ጥያቸው እንዳልሄድ እኔም ስጋት ላይ ነኝ" ይላሉ በላስ ቬጋስ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አበራሸ ኦሮሞ የተባሉ የሦስት ልጆች እናት። "ባለቤቴ ልጆቼ ፊት ነው ትንፋሽ አጥሮት ሕይወቱ ያለፈው ፤ ቤተሰቤን ከባድ መከራ ውስጥ የከተተ ሐዘን አድርሶብኛል" ብለውናል ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:11:20 0:00

በሌላ በኩል በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በበኩላቸው በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ፤በሕክምና አገልግሎት መስጫ ቦታ ላይኢትዮጵያውያ በዛ ብለው ስለሚገኙ፣ አረጋውያንንበመንከባከቢያ ቦታ እንዲሁም አስፈላጊ በሚባሉት ያልተቋረጡ አገልግሎት መስጫ ዘርፍ ውስጥ የሚሰሩ በመሆናቸው በወረርሽኙ ሰለባዎች ከሆኑት ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል። ቁጥሩ ሲመዘገብም አብዛኞቹ አፍሪካን አሜሪካን በሚል የተመዘገቡ ቢሆንም በየቦታው የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ፣እድርናየመሳሰሉት የተለያዩ አደረጃጀቶችን ተጠቅሞ ኢምባሲው ባገኘው መረጃ እስካሁን 100 ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ -ኢትዮጵያ ህይወታቸው ማለፉ ይህንንም መስማት እጅግ ከባድ ሐዘን መሆኑን ተናግረዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና - ትውልደ ኢትዮጵያ ሁሌም ሐሳባቸው አገራቸው በመሆኑ በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በባለሞያ ምክረሐሳብ በከፍተኛ ሁኔታ አገራቸውን እያገዙ መሆኑን ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በስካይፕ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG