እስክንድር ነጋ በሕትመት ጋዜጠኝነት ለረጅም ዓመታት ሠርቷል። በሰርካለም አሳታሚ ይታተሙ የነበሩ ምንሊክ፣ አስኳል እና ሳተናው ጋዜጦችን ያዘጋጅ ነበር። ከስምንት ጊዜ በላይ ለእስር ተዳርጓል። ከስድስት በላይ ሐሳብን ከመግለፅና ከመጻፍ ነፃነት ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ተቀብሏል። አሁን የኢትዮጲስ ጋዜጣ ባለቤት ነው። ከአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እንቅስቃሴ የሚያደርግ የባላደራ ምክርቤትም ሰብሳቢ ነው።
“የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከያና መቆጣጠሪያ ረቂቅ ዐዋጅ” ፤ ተጨማሪ ውይይት ሳይደረግበትና ሳይከለስ ባለበት ሁኔታ ከፀደቀ ሐሳብን የመግለጽ ነፃነትን ይጋፋል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ።
ከታኅሣሥ 6 እስከ 8/ 2012 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ከመላው ዓለም የተውጣጡ ስደተኞችና 750 ልዑካን ቡድን አባላትን ጨምሮ ወደ 3ሺሕ ሰዎች ጀኔቫ ውስጥ በዓለም ላይ ስላሉ ስደተኞች ለመምከር፣ ሐሳብ ለመለዋወጥ እና የገንዘብና የዓይነት እና የስልት የእርዳታ ቃሎችን ለማሰባሰብ ተቀምጠው መክረዋል።
በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ ባንድ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውና ከ1973 እስከ 1986 ዓ.ም ከ250 በላይ የሙዚቃ አልበም የሠራው አይቤክስና ሮሃ ባንድን ከመሰረቱት መካከል ሁለቱ የጋቢና ቪኦኤ እንግዳ ነበሩ። ቤዝ ጊታር ተጫዋቹ ጆቫኒ ሪኮና ባለ ሊድ ጊታሩ ሰላም ስዩም ልምዳቸውን አካፍለውናል። (ውይይቱን ተከታተሉ)
ከኡስታዝ አቡበከር አሕመድና ከቀሲስ ደረጀ ስዩም ጋር ኢትዮጵያውያን እና ሃይማኖታዊነት ፣ ሃይማኖትና የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና የሃይማኖት ተቋማት ወቅታዊ ቁመና ላይ የሚያተኩር ውይይት አካሂደናል። (በዚህ በክፍል ሁለት ውይይት ሃይማኖትና የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና የሃይማኖት ተቋማት ወቅታዊ ቁመና ተነስቷል ተከታተሉት።)
ከኡስታዝ አቡበከር አሕመድና ከቀሲስ ደረጀ ስዩም ጋር ኢትዮጵያውያን እና ሃይማኖታዊነት ፣ ሃይማኖትና የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና የሃይማኖት ተቋማት ወቅታዊ ቁመና ላይ የሚያተኩር ውይይት አካሂደናል። (ለዛሬ ኢትዮጵያውያን እና ሃይማኖታዊነት የተመለከተውን የመጀመሪያ ክፍል ይከታተሉ)
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ የተወሳሰበ በመሆኑ የሚያስፈልጋትም የተወሳሰበው የሚፈታ፣ ጠንካራና የተጠና መፍትሔ ሊሆን እንደሚገባው በዋሽንግተን ዲሲ ለውይይት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ገለፁ።
በምስራቅ ሐረርጌ ሁለት አብያተ ክርስቲያን እና የክርስትና እምነት ተከታይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ በምዕራብ ሐረርጌ ደግሞ አንዲት ሴት መገደሏን እና መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎችና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን አስተዳዳሪዎች ገልፀዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በቡድን በሚንቀሳቀሱ ወጣቶች መሆኑንም ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የ2012 ኖቤል የሰላም ሎሬት ኾነው መመረጣቸው ከተሰማ በኋላ ከመላው ዓለም የሚላኩ የደስታ መግለጫዎች ማኅበራዊ ሚዲያን በተለይም ደግሞ ትዊተርን አስጨንቀውት ውለዋል። የአገር መሪዎች፣ ታዋቂ የፖለቲካ ሰዎች፣ አምባሳደሮች በአጠቃላይ “ቀዳሚ” በሚባል ዘርፍ የሚሰለፉ አብዛኞቹ መልዕክታቸውን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰደዋል።
የኖርዌይ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው አሸናፊነታቸውን ይፋ ባደረገበት መግለጫ ፤ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሰላምና ለዓለም አቀፍ ትብብር ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት የሽልማቱ አሸናፊ መሆናቸውን አብስሯል።
ለዛሬ በአስቸኳይ ተጠርቶ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ነገ እንደሚቀጥልና በመጨረሻም አጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱን አቋም የሚያንፀባርቅ መግለጫ እንደሚወጣ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያ ተልኮ መመሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ ሰላም ቀሲስ ሰለሞን ቶልቻ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
ሰሞኑን አከራካሪ በሆነው የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ማቋቋም ጉዳይና ወቅታዊ ሁኔታ እንዲወያይ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ለሐሙስ ተጠርቷል ተብሏል።
የመተማ ዮሃንስ አካባቢ የመከላከያ አዣዥ ሳያውቅ ጥይት ጭነው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ የነበሩና “የሠራዊቱ ንብረት ናቸው” የተባሉ አምስት የጭነት ተሽከርካሪዎች በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የተመረቱና በሕጋዊ ሰነድ የተሸጡ መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል አሕመድ ሐምዛ ገለፁ።
የመተማ ዮሃንስ አካባቢ የመከላከያ አዣዥ ሳያውቅ ጥይት ጭነው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ የነበሩ “የሠራዊቱ ንብረት ናቸው” የተባሉ አምስት የጭነት ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል - ምዕራብ ጎንደር ብርጌድ አዣዥ ኮለኔል ሰለሞን አሻግሬ አስታወቁ።
• እሁድ ጁላይ 21 ጠዋት አፍሪካውያን ለሩጫ ይሰባሰባሉ ተብሏል • አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ይሸለማሉ (የውድድሩ ዋና አዘጋጅ ዶ/ር ጋሻው አብዛ ስለ ዝግጅቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል)
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት አቶ ንጉሱ ጥላሁን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ዋሽንግተን ዲሲ በነበራቸው ቆይታ ከአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ ጋር አጭር ቆይታ አድርገው ነበር። የመጀመሪያውን ክፍል ባለፈው ሳምንት አቅርበንላችሁ ነበር። ክፍል ሁለቱን ተከታተሉት።
የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ከሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ከሆኑት አቶ ነቢያት ጌታቸው ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡(ክፍል አንድ)
በመጭው ዓመት ሊደረግ የታቀደውን ጠቅላላ ምርጫ ጊዜ ፤ መራዘምም ሆነ አለመራዘም በተመለከተ ለማንም መግለጫ ሰጥቶ እንደማያውቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ከማኅበራዊ ሳይንስ መምሕሩ ረዳት ፕሮፌሰር ደረሰ ጌታቸው (ዶ/ር)ጋር ስለ ማኅበረሰብ ተግባቦት የተደረገ ቃለ ምልልስ። ( ከፍል ሁለት)
ቃለ ምልልስ ከማኅበራዊ ሳይንስ መምሕሩ ረዳት ፕሮፌሰር ደረሰ ጌታቸው (ዶ/ር) (ክፍል አንድ)
ተጨማሪ ይጫኑ